ሰኔ 16፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞን ግበሬዎች እና ነጋዴዎችን የኦኮኖሚ ጥገኛ ለማድረግ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውንና ሱቆቻቸውን ከነንብረቱ ከማቃጠል አልፈው ለእርሻ ግብዓቶች መግዣ፣ ለልጆቻቸው የትምህርት ቤት ወጪዎች መሸፈኛ፣ እንዲሁም ለተለያየ ወጪዎች ቆጥበው እራሳቸው በመረጡት ባንክ ያስቀመጡትን ገንዝብ የብልፅግናው ቡድን ካድሬዎች ወደ መሰረቱት ባንክ እንዲያዘዋውሩ በአፈ ሙዝ በማስገደድ ላይ ይገኛሉ። ይህም ድርጊት የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በቀላሉ ገንዝባቸውን በፈለጉበት ግዜ እና መጠን ለማውጣትም እንዳይችሉ በቀላሉ ለማገድ እንዲመቻቸው ያቀዱት ዙዴ እንደሆነና በሰፊው በኦሮሚያ ውስጥም በሰፊው በመተግበር ላይ ይገኛል።
በዚሁ መሰረት በምዕራብ ባሌ ዞን አርና ቡሉቅ ወረዳ ውስጥ ገበሬዎችን እና ነጋዴዎችን በኮሜርሻል ባንክ እና በአዋሽ ባንክ ውስጥ የነበራቸውን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ወደ ሲንቄ ባንክ እንዲያዘዋውሩ የተወሰነ የግዜ ገደብ እንደተሰጣቸውም የአቢኦ ምንጮች አረጋግጠውልናል።
ከዚህም ሌላ በወረዳው ውስጥ የሚያገለግሉ መሞህራን ደሞዝ እየቀነሱ እንደሚከፈላቸውና በዚህም ምክናያት የኑሮ ውድነትን መቋቋም እንዳቃታቸው
ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀውልናል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
