ሰኔ 16፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ዳቦ ሃና ወረዳ
የማፍያው ብልፅግና ጦር ወጣቶችን አፍሶ በመያዝ ጭካኔን በተካኑ የግፍ ስቃይ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲተገብሩ ሆን ብሎ ባሰለጠናቸው ሰራዊት እያስደበደበና ፀጉራቸውን በደረቁ እያስላጨ ማሰቃየቱን ቀጥሏል። ይኸ እኩይ ወንጀል ጠፍጥፎ ከመሰረታቸውና የኢህአዲግ መንግስት የወረሱት ሲሆን፣ በጋራ በማህበረሰቡ ላይ ሲፈፅሙ እንደነበረ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው።
ግንቦት 14፣ 2024 የፋሺስት ብልፅግና ቡድን ጦርም የፈጣሪያቸውን የስልጠና ክህኖት በመከተል በከኔ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ወጣቶችን በመያዝ ችግራቸውን በደረቁ መላጨታቸውን የአቢኦ ምንጮች ገልፀዋል። ከዚህም ሌላ ከሳምንት በፊት ሞተር ሳይክል በመንዳት የሚተዳደሩትን ሰዎች በጠቅላላ በመሰብሰብ ፀጉራቸውን በደረቁ ላጭተው በድብደባ ሲያንገላቷቸው መቆየታቸው ታውቋል።
ሚያዚያ 29፣ 2024 በሐሩ ብራኑ የተባለ ቄሮንም በዚሁ ከኔ ከተማ ውስጥ ይዘውት በጠርሙስ ስባሪ ፁጉሩን ከላጩት በኋላም ለሁለት ሳምንት ያህል በእስር ቤት ሲያሰቃዩት ቆይተዋል።
በወረዳው ውስጥ “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ” በሚል ሰበብና የሃሰት ውንጀላ በነፃ የመንቀሳቀስ ነፃነት በመገደብ ነዋሪዎች እንደፈለጉት ወጥተው መግባት የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውንና ለአቢኦ ዘግበዋል።
ጨዋቃ ወረዳ
የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን ግንቦት 13፣ 2024 በገቢና ቀበሌ የሰርግ በዓል ታዳሚ በነበረው ህዝብ ላይ ተኩስ በመክፈት፣ 31 ሰዎችን ይዘው ሄደዋል። እስር ቤትም ካቆዩዋቸው በኋላ ወደ ጦር ሜዳ ስልጠና ለመላክ አንድ ቦታ ላይ እንደሰበሰቡዋቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
