ሰኔ 25፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ግፈኛው የብልፅግና ማፍያ ቡድን በመላው ኦሮሚያ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ይቅር የማይባል ወንጀል እየፈፀመበት ይገኛል።
የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን ግንቦት 14፣ 2024 የኑሮ ውድነቱን በመቋቋም፣ ወላጆቻቸውን የሚረዱና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳደሩ ኦሮሞዎችን በግዳጅና በገፍ እያፈሱ ወደ ጦር ካምፓቸው እያጋዙ ይገኛል። ይህንንም ድርጊት በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን፣ በበደኖ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች ውስጥ እየተገበሩት መሆኑንም ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን በአጠቃላይ በማንኛውም አካባቢ የተጎሸመው የጦርነት ነጋሪት የኦሮሞ ህዝብን የማይመለከት መሆኑን ቢረዳም በግልፅ የጠመንጃ አፈሙዝን ወደ ፊቱ እያሳየ ለሚያፍሰው የፋሺስት ጦር እምቢታውን የሚገልፀው ጥቂት ነው። የጦር ዘመቻው አይመለከተንም ልጆቻችንን፣ ጠዋሪዎቻችንን አትወስዱም ያሉት ለጊዜው ገንዘብ ካላቸው በመዝረፍ የሌላቸውን ደግሞ አስረው በማሰቃየት ላይ እንዳሉ ከምንጮቻችን መረጃው ደርሶናል።
በዚህም መሠረት ልጄን ወደ ጦርነት አልልክም ያሉትና የገንዘብ ቅጣት ለልጃቸው ከከፈሉት መሃከል ስማቸውን ያገኘነው፦
- ከኢብሳ ጀማል 10,000 ብር፣
- ከመሐመድ ሙሳ አሜ 7000፣
- ከጫላ ኡመር 10,000፣
- ከጀማል አብዲ 12,000፣
- ከኡስማ ኡስማኢል አሊ 10,000፣
- ከሹክሪ ሮባ 8000፣
- ከኢምራን መሐመድ ዩሱፍ 9000፣
- ከታጁዲን ሱፊያን 9000፣
- ከጫልቱ ደቻሳ 9000፣
- ከኢብራሂም አህመድ ሙሳ 7000፣
- ከጋዲሳ በከር አሊ 9000፣
- ከባሩዲን ሱፊያን 10,000፣
- ከዩሱፍ ሻፊ 15000፣
- ከጫላ አሊዬ 15000 ሲሆን፣ በርካታ ሰዎች ላይ ይህ ዘረፋ እንደተፈጸመና ዘረፋውም እንደቀጠለ ገልጸውልናል።
ይህ ድርጊት በምዕራብ ሐረርጌ ዞንም እየተገበሩት ይገኛል። ይህም የአፈሳ ዘመቻ በዝናብ እጦት (በድርቅ) የሚቸገረው ህዝብ የበለጠ ችግር ውስጥ እንደሚያስገባቸው በመገንዘብ ህብረተስቡ ጭንቀት ውስጥ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልጸዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
