ሐምሌ 14፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን፣ ሱሉላ ፊንጫ ወረዳ የስኳር ፋብሪካው አከባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የአምባገነኑ እና የፋሺስቱ አብይ አህመድ ጦር ቡድን ወቅታዊ የግብርና ስራቸውን እንዳይሰሩ ከማገዳቸውም በላይ አርሶ አደሮቹን በማሰቃየትና በማስፈራራት ላይ እንዳሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
አክለውም በእርሻ ቦታው ላይ የተገኘ ማንኛውም ገበሬ በገዳይ ጦር ቡድን በጥይት ተመትቶ እንዲገደል የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን እንደወሰነም ገልፀዋል።
ልጆቻችሁ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እና የኦሮሞ ነፃነት ቄሮ አባል ናቸው በማለት የታጋይ ቤተሰቦችን ማሰቃየቱንም ቀጥለውበታል። እራሳቸውን ለማሸሽ የሚጥሩትን በወንዝ ዳርቻዎች ሳይቀር እያሯሯጡም በመያዝ ክፉኛ ከመደብደብ፣ ከማሰርና ከማሰቃየት በላይም ቤት ንብረታቸውን በእሳት እያጋዩ ማውደምንም በሰፊው ቀጥለውበታል።
በቁጥር በርካታ የሆኑ ሰዎችም ከቀዬአቸው ተፈናቅለዋል። በአጠቃላይ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን አርሶ አደሮች ወቅታቸውን ጠብቀው ማረስ በመከልከላቸው ለመጪው ወራቶች እና አመታት የሰው እጅ ጠባቂ እና ተመፅዋች የሚያደርጋቸው በመሆኑ እንዳሳሰባቸው ለአቢኦ ገልፀዋል።
#የፋሺስት_አብይአህመድ_ሰራሽ_ረሃብ በቅርቡ ያበቃል
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
