ሐምሌ 22፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኢምፓየርቷን ህገ-መንገስት እና ደምብ እራሱ ሳያከብር ግለሰቦችን ህግ ጥሳችኋል በማለት ጭካኔ የተሞላበት የጦር ወንጀል በየቀኑ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለው የብልፅግና ጦር ቡድን በተለያዩ ምክንያቶች የጅምላ እስሩን እና ከእስር ቤት እያወጣ መረሸኑን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ሐምሌ 9፣ 2024 በምስራቅ አርሲ በጀጁ ወረዳ፣ በሀቡሌ እና በስምፒጤ ፊንጮ ቀበሌ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎችን ከስራ ቦታቸው ድረስ በመሄድ ከያዙዋቸው በኋላ ምን ስታደርጉ እንደነበር ተናገሩ በማለት እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገሩ።
ተይዘው በወረዳው እስር ቤት ውስጥ ታጉረው እየተሰቃዩ ካሉት ሰዎች ውስጥ ስማቸው ለጊዜው የደረሰን፦
- ኦቦ አብዱረማን ጀይላን
- ኦቦ አረባ ሀጂ ሀምሳ
- ኦቦ ሲራጅ አረባ እና
- ኦቦ ታካላ ናቸው።
እነዚህም ሰዎች ከባድ ስቃይ ውስጥ መሆናቸው እና ቤተሰቦቻቸው ሄደው እንዳያናግሯቸው የወረዳውን ፖሊስ ጣቢያ በሚጠብቁት የፋሺስት አብይ ታጣቂዎች መከልከላቸውም ታውቋል።
በወረዳው ውስጥም ከተለያየ አካባቢ አምጥተው ያሰርዋቸውን ኦሮሞዎች ከእስር ቤት እያወጡ መረሸናቸውን ቀጥለዋል። ይኸውም አንድ መኖሪያ አድራሻዋ እና ስሟ ያልታወቀ ቀሬ ሐምሌ 8፣ 2024 ሶቄ ቦቂቻ ቀበሌ ውስጥ በፉሺስት ብልፅግና ገዳይ ጦር ቡድን ተገድላ መጣሏን የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናገረዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎች አክለውም ቀሬዋ ዶኒ ከተማ እስር ቤት እንደነበረች እና ከዚያም አውጥተው በመኪና ቀበሌአቸው ድረስ አምጥተው ከመኪናም አውርደው እንደገደልዋትና እንደሄዱ ተናግረዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
