ነሐሴ 1፣ አራታ በዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በኦሮሞ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ስራዬ ብሎ የተያያዘው የፋሺስት አብይ ብልፅግና ቡድን ጦር በምስራቅ ሸገር ዞን፣ በቦራ ወረዳ በኦሮሞ ህዝብ ሀብት በተገዛ የጦር መሳሪያ ያስታጠቀው ሽብርተኛውን የአማራ ፋኖን ብቻ ሳይሆን አማራ የሆኑትን ሰዎችንም እየመረጠ በማስታጠቅ ኦሮሞዎች ላይ አሰቃቂ ግድያ እና ዘረፋ እንዲፈፅሙ እያደረገ መሆኑን ምንጮች ለአቢኦ ተናገሩ።
በፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን የታጠቁ ፅንፈኛ የአማራ ፋኖን ፈለግ የሚከተሉም የአካባቢው ሰፋሪዎች በሰላማዊ ማህበረሰብ ላይ በተደራጁበት መስክ አሰቃቂ ግድያ እና ዝርፊያ ከሐምሌ 2 እስከ 5፣ 2024 መፈፀማቸውን የዓይን እማኞች ለአቢኦ ተናግረዋል።
በረታ ሳሚ ቀበሌ
ቄሮ ፋጆ ቡታን “ከ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለህ” በማለት ከመኖሪያ ቤቱ አውጥተው በቀበሌው ውስጥ በመግደል አሰከሬኑን እንኳን ቤተሰቡ እንዳይወስድ እንዳደረጉ የቀበሌው ነዋሪዎች ተናገሩ።
በተጨማሪም ስማቸው ያልተለየ ሁለት ቄሮዎችን በመግደል አስከሬናቸውን በባርታ ሳሚ ቤተክርስቲያን ውሰጥ እንደጣሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለአቢኦ ተናግሮዋል። እነዚህ የአማራ ታጣቂዎች በቦራ ወረዳ ባርታ ሳሚ ቀበሌ ገብርኤል በሚባል ቤተክርስታን ውስጥ ካምፕ እንደመሰረቱና በየቀኑም የኦሮሞ ልጆችን ደም እያፈሰሱ እንደሆነ ገልጿል።
ጅርሜ ቦራ ቀበሌ
ተሹ ለማ የተባለ ቄሮን አፍነው ወስደው፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደሉት በኋላ አስከሬኑን እዚያው እንዳቃጠሉት ከቀበሌው ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ሰው ተናግሯል።
ይህንን አሰቃቂ ወንጀል በኦሮሞዎች ላይ እንዲተገበር የማቀናጀት ስራውን የሚያከናውኑት ሰዎች፦
- ወንዱ ሀሰን የባርታ ቀበሌ ሊቀመንበር/አስተዳዳሪ
- ደጀኑ እሼቱ የወረዳው ካድሬ/ካቢኔ
- አሰባ ከበዳ የወረዳው ደህንነት ሲሆኑ፣
እነዚሁ ግለሰቦች በሌሊት ኦቦ ኢፋ ቶላ የተባለ ሰው ቤት ዘራፊዎችን በመላክ 60,000 ብር አዘርፈዋል። ከዚህም በላይ የቀበሌውን ህዝብ ለእኛ ቤት መስራት አለባችሁ በማለት እያስቃዩዋቸውም እንደሆነ የቀበሌው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ፣ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ወይም ሬሳቸው እንዲቃጠል ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
