ነሐሴ 5፣ አራታ በዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የፋሺስት ብልፅግና ቡድን ከወራት በፊት ባወጣው መግለጫ መሰረት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቤተስቦችን መዝረፍ፣ ቤት ከነንብረቱ በእሳት ማውደም፣ በድብደባ አካለ ጉዳተኛ ማድረግ፣ ማሰር እና ማሰቃየት፣ በአሰቃቂ መንገድ መግድልም አልበቃ ብሎዋቸው ጨቅላ ልጆቻቸውን ጠልፈው መሰወርም ጀምረዋል።
ሐምሌ 10፣ 2024 በጀልዱ ወረዳ፣ ክልቤ ቀበሌ ውስጥ የብልፅግና ጦር ቀብሶ ደበላ የተባለውን የሰባት ዓመት ህፃን አባቱ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ በመሆኑ ምክንያት እናቱ አትውሰዱብኝ ብላ ብትለምንም ይዘውት ሄደዋል። የህፃኑም እናት ልጇን ልትጠይቅ የጦር ካምፓቸው ሄዳ ብትጠይቅም ልጇን ሳያሳይዋት እንዲሁም አሰፈራርተዋት እንደተመለሰች የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል። ቀጥለውም ልጁን በመሰወራቸው ምክንያት በህይወት መኖሩንም ሆነ አለመኖሩን ለማወቅ አልተቻለምም ብለዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ እና የብልፅግና ቡድኑ የኢምፓየሪትዋ ሆነ የአለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ህግጋቶችን በመጣስ እና በጦር ወንጀለኛነቱ በህግ ፊት ቀርቦ ተጠያቂ መሆኑ የማይቀር ነው።
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ መልኩም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሎአል።
