• Wed. Nov 25th, 2026

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሰሜን ሸገር ደገም ወረዳ ውስጥ ጠላትን ሙት እና ቁስለኛ አድርጎ ሸኝቷል

Aug 8, 2024

ነሐሴ 8፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በፋሺስት የብልፅግና ጦር ላይ የሚወስደውን የማያዳግም እርምጃ በማጠናከር አኩሪ ድል እያሰመዘገበ ይገኛል።

በዚሁ መስረት ሐምሌ፣ 26 ቀን በሰሜን ሸገር ዞን፣ ደገም ወረዳ፣ በአሊ ዶሮ ቀበሌ ውስጥ ፊንፊኔን እና የአማራ ክልልን በሚያገናኘው ትልቁ አውራ ጎዳና ላይ በአንድ ፓትሮል ሲጓዙ የነበረ የፋሽስቱ ብልፅግና የጦር መኪና ላይ በወሰደው አድፍጦ የማጥቃት እርምጃ ሰድስት ጠላትን ወዲያውኑ ገድሎ አራቱን በማይሽር ቁሰል ሸኝቷል። 

በመሳሪያ በኩልም ሁለት AKM ከሙሉ ትጥቅ ጋር ከላያቸው ላይ ፈትቶ ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርጓል።

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ለህዝቡ ነፃነት የሚያደርገዉ ትግል አጠናክሮ ይቀጥላል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!

Leave a Reply