ነሐሴ 12፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የጦር ወንጀልና የሰብዓዊ መብት ረገጣን የሚያካሂደው የፋሺስት አብይ አህመድ የጦር እና ካድሬ ቡድን በየመስካቸው የስልጣን ዘመናቸውን ለማራዘም የሚቀምሩት ስልት ውጤት አልባ እየሆነ እና እየተጋለጡ ይገኛሉ።
በምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ቂልጡ ካራ ወረዳ
ሐምሌ 18፣ 2024 የፋሺስት ብልፅግና ጦር ቡድን ሰው ሰራሽ ፀጉር በማድረግ በወንዲ ዳሌ እና ቡኬ አካቼ የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በመሰማራት እኛ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ነን በማለት ህዝቡን ለማታለል እየሞከሩ መገኘታቸውን አቢኦ ከምንጮቹ አገኘ።
ምሥራቅ ሀረርጌ ዞን፣ በደኖ ወረዳ
የፋሺስት ብልፅግና እፋኝ የጦር ቡድን ከካድሬዎቹ ጋር በተቀናጀ መልክ ቄሮ እና ቃሬዎችን በሃሰት ተስፋ ወደ እራሳቸው ካቀረብዋቸው በኋላ እየሰወሩዋቸው እንደሆነ ታውቋል።
ሐምሌ 16፣ 2024 የብልፅግና አስተዳደር ክፍል ጎሮ ዋዶ ቀበሌ ውስጥ ወጣቶችን አንድ ላይ በመሰብሰብ አያባበሉ እንደዋሉ ስብሰባውን የተካፈሉ ለአቢኦ ተናግረዋል። “በ2017 (በኢምፓየሪትዋ አቆጣጠር) ለስራ አጦች በሙሉ ስራ እንሰጣለን ስለሆነም ከመዋቅራችን ጋር ሁኑ እና ስሩ።” ብለው ለማታለል እንደሞከሩም የስብሰባው ተሳታፊዎች አክለው ገልፀዋል። ያለው እውነታ የዚህ ተቃራኒ ስለሆነ ቄሮና ቃሬ ከእንደዚ ዓይነቱ የማታለያ ዘዴ እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#የሺኒጋው_ቃልኪዳን_ዘመቻ ይቀጥላል!
የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ያወጀው የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ዘመቻ ጦርነት የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት እና የሀገር ባለቤትነት እስኪረጋገጥ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል።
