• Tue. Nov 24th, 2026

የአብይ አህመድ መራሹ መንግስት ታጣቂ ሃይሎችና አጋራቸው የአማራው ፅንፈኛ ፋኖ በኦሮሚያ አሰቃቂ ግድያና የሰብአዊ መብት ረገጣን በመናበብ እየተገበሩት ይገኛሉ

Mar 14, 2024

መጋቢት 14/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

‘የአባቶቻችንን ታሪክ እንደግማለን’ በሚል ፉከራ ልክ እንደ ቀደምት አባቶቻቸዉ የአንድ ቋንቋ፣ የአንድ ባህል፣ ሀገርና፣ የአንድ ሃይማኖት ስርኣትን እንመልሳለን በማለት ፋኖ ብለዉ ራሳቸዉን ያደራጁትና በጸረ-ኦሮሞ አቋማቸዉ በአብይ አህመድ ቡድን የሚደገፉት ጽንፈኞች በኦሮሞ ህዝብ ላይ ባወጁት የዘር ፍጅት እጅግ ከፍተኛ የሚባል የሰው ህይወትና ንብረት እየጠፋ ይገኛሉ። 

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አቤ ዶንጎሮ ወረዳ በአማራ ፋኖ ታጣቂዎች ሰላማዊ ዜጎች መገዳላቸዉና ንብረት መዘረፉ እንደቀጠለ ነዉ። መጋቢት 8 ቀን 2024 ፈዬራ ቶሌራ  የተባሉ አዛውንት በዳለቾ መንደር ወደ ስራ ገበታቸዉ እየሄዱ ባሉበት ወቅት በግፍ ተገድለዋል። በኢዶ ኩሳ ልዩ ስሙ አንዶዴ በሚባል ስፍራም ታጣቂዎቹ የኦቦ ቤንኩ አብዲን ቤተሰብ፣ ባለቤታቸውንና ልጃቸውን በአንድ ቦታ ካረዱ በኃላ የቤት እንስሳትንና ንብረቶችን ጨምረዉ ዘርፈዋል። ነዋሪዎቹ አክለዉም እነዚህ የአማራ አማፂ ቡድኖች በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ከመራሹ አብይ መንግስት ጋር በመተባበር ስልጠና እየወሰዱ እንደሆነም ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

ከዚህም በላይ ብልጽግና እያለ ራሱን የሚጠራዉ ጸረ-ኦሮሞ ቡድን መጋቢት 10/2024 በምዕራብ ወለጋ ዞን ቂልጡ ካራ ወረዳ ለሊሳ ኮምሲ ቀበሌም ጥበቡ ኦወታ የተባለን ግለሰብ በጭካኔ ረሽኗል። ጥበቡን ከገደሉ በኋላ ቡርቃ Dhiቢሳ የተባለን ወጣትም ይዘው መሄዳቸውን የአከባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል::

የኦሮሞ ህዝብ ጠላቶች በየፊናቸዉ በትብብር ዘምተዉብን ባሉበት በዚህ ሰዓት ህዝባችንም አንድነቱን የበለጠ በማጠናከር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር በመሆን ትግሉን ማፋፋም ይጠበቅበታል።

አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

Leave a Reply