• Wed. Nov 25th, 2026

የኢምፓየሪቱ  ጠባቂ ኃይሎች በኦሮሚያ ማዕከላዊና ደቡብ ምሥራቅ ዞኖች ውስጥ ግድያ እሥራት ዝርፊያና ቤትን ከነንብረቱ ማጋየት አጠናክረው ቀጥለዋል

Mar 14, 2024

መጋቢት 14/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

ቤትንና ንብረትን ማቃጠልና በጥርጣሬ ብቻ የኦሮሞን ሕዝብ ወደ እሰር ቤት ማጎር በመላው ኦሮሚያ እንደቀጠለ ነው። መንግስት ነኝ ባዩ ቡድን በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እየደረሰበት ያለዉን ሽንፈት ለመበቀል በሚመስል መልኩ ሰላማዊ ዜጎችን እየገደለ፣ እየደበደብና እየዘረፈ ይገኛል። ከሁለት የኦሮሚያ ዞኖች የመረጃ ምንጮቻችን ያደረሱንን በሚከተለዉ መልኩ አጠናክረናል።

መጋቢት 8/2024 በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ሻናን ኮሉ ወረዳ ዜጎች ‘የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ትቀልባላችሁ’ በሚል ክስ ወደ እስር ቤቶች እየታጎሩ ነዉ። በዞኑ ዉስጥ የተሰማራውም ጨካኝ ሰራዊት ኡንኬ ቀበሌ ውስጥ ከየትኛዉም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ገለልተኛ በመሆን የእለት እለት ኑሮዋቸውን እየገፋ የነበሩ ኑዋሪዎችን ‘የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን ትቀልባላችሁ፣ መንገድ ታሳያላችሁ፣ ጥቆማ ትሰጣላችሁ’ በማለት ወንጅለው እስር ቤት አጉረዋቸዋል። ከታሰሩት መካከል  ስማቸዉን ያገኘነው  ሃሊማ ሃጂ፣ አዳሞ አብደላ፣ በሻቱ አህመዲን፣ ሞኣዝ አብደላ ሓሰኔ ጥቂቶች ሲሆኑ ለጊዜዉ ስማቸውን ማግኘት ያልተቻለ ነዋሪዎች ይገኙበታል።

በተመሳሳይ መልኩ መጋቢት 9/2024 በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ቶሌ ወረዳ የፋሽስቱ ብልፅግና ወታደሮች የአርሶ አደር ኡርጌሳ ደገፋ ኦዳን መኖሪያ ቤት ከነሙሉ ንብረቱ በእሳት አጋይተዋል። በዚህም ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎቻችን በአሁኑ ወቅት ለጥገኝነት ኑሮም እየተጋለጡ ይገኛሉ። በዚህ ወረዳ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ድብደባ በርካቶች መጎዳታቸውንና ብዙዎችም እንደታሰሩ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

ሕዝባችን አንድነቱን የበለጠ በማጠናከርና ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጋር በመተባበር በጫንቃው ላይ የተጫነበትን የባርነት ቀንበር ማራገፍ ዘላቂ መፍትሔዉ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርበታል።

Leave a Reply