• Sun. Mar 15th, 2026

ፋሽስቱ የአብይ አህመድ መንግሥት ራሱ አደራጅቶ በኦሮሞ ህዝብ ሀብት በተገዛ የጦር መሣሪያ ባስታጠቀው ፋኖ ብሎ ራሱን በሚጠራ ፅንፈኛ ቡድን የወሎን ኦሮሞ እያስጨፈጨፈ ይገኛል

Mar 17, 2024

መጋቢት 17/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በኦሮሞ ህዝብ አንጡራ ሃብት የጦር መሳርያዎችን ገዝቶና ሰራዊት አደራጅቶ ኦሮሚያን ለማፍረስ በአማራ ጽንፈኞች እየታገዘ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ዘምቶ ያለዉ የአብይ አህመድ ቡድን ከምን ጊዜዉም በላይ በኦሮሚያ፣ በወሎ ሰሜን ኦሮሚያንም ጨምሮ የሚፈጽመዉን ግፍ አጠናክሮ ቀጥሏል።  

ይኼ ፋኖ ብሎ ራሱን የሰየመዉ የድሮ ሥርዓት ናፋቂ ቡድን በሰሜን ኦሮሚያ ወሎ ዞን ላይ የከፈተዉንም ጥቃት በመቀጠል መጋቢት 11/2024 በጂሌ Dhuሙጋ ልዩ ስሙ ኬላሼ በተባለ ሥፍራ የ6 ሰዎችን  ሕይወት ቀጥፎ በ10 ሰዎች ላይ ከባድ የመቁሰል አደጋ ሲያደርስ በህዝብ ንብረት ላይ ዝርፍያና በእሳት ማጋየት ድርጊትም ፈጽሞኣል። በዚህም ዕለት ከተገደሉትና ክፉኛ ከቆሰሉት ኦሮሞዎች መሃከል ስማቸው የደረሰን የሚከተሉት ናቸው፦

በጭካኔ ከተገደሉት

  1. ሰኢድ አህመድ አባዬ
  2. ጀማል ጦይብ
  3. አርብ አልዪ
  4. ሰዒድ ሞሐመድ እባጋር እና
  5. አሊዪ ተስፌሁን ንጉስ ሲሆኑ

ክፉኛ ከቆሰሉት

  1. ሙሄ ኑርዬ
  2. እያሱ አሊዪ
  3. አህመድ ዑመር
  4. ሼህ ሁሴን አህመድ
  5. ሡልጣን አባ አሊ
  6. አሂመድ ሞሐመድ አሊቶ
  7. አዳም ዑስማን
  8. ሰዒድ አሂመድ ዘራፍ እና
  9. አሊዮ ሃሳኑ ናቸው።

የአከባቢዉ ሰዎች እንደገለጹት ትንኮሳዉ ዛሬም የቀጠለ ሲሆን ተጨማሪ ኃይል ከኋላቸው እየጠሩ ከመሆናቸዉም በላይ በውጊያዉ ምክንያት መንገድ በመዘጋቱ በዚህ የፆም ወቅት ለህዝባችን የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ሸቀጦችን ማስገባት ባለመቻሉ ለተጨማሪ ችግር ተጋልጠዋል ።

የኦሮሞ ህዝብ ጠላቶች በየፊናቸዉ በትብብር ዘምተዉብን ባሉበት በዚህ ሰኣት ህዝባችንም አንድነቱን የበለጠ በማጠናከር ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር በመሆን ትግሉን በማፋፋም ከዚህ የባርናት ቀንበር መላቀቅ ብቻ ዘላቂ መፍትሔዉ እንደሆነ ይታመናል።

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading