• Sat. Sep 26th, 2026

የዕድሜ ገደብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የማይገባው የአብይ አህመድ መራሹ ቡድን ህፃናትን፣ ወጣቶች እና አረጋዊያን (የሀገር ሽማግሌዎች) በእስር ቤቱ ዉስጥ ማስቃየቱን ቀጥሏል

Mar 23, 2024

መጋቢት 23/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኢትዮጵያን ኢምፓያር ከውድቀት ለማዳን የሚታታረው አሸባሪው የብልፅግና አመራር ንፁሃን እና የህዝብ ዓይን ወይም አለኝታ እንዲሁም የነገ ተስፋ የሆኑ የኦሮሞ ወጣቶችንና ሌሎች ንጹሃን ግለሰቦችን በጥርጣሬ ዓይን በማየት እስር ቤት እያጎረ እንደሚያሰቃይና ሌሊት ሌሊት ከእስር ቤት እያወጣ በመግደል ሬሳቸውን ሜዳ ላይ በመጣል በአውሬ እያስበላና የቀሩትን እስር ቤት ውስጥ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለረጅም ወራቶች አስሮ እያሰቃየ ይገኛል።

አሸባሪው የብልፅግና ቡድን በድብቅ እስር ቤት ዉስጥ በቁጥር ብዙ የሆኑ የኦሮሞ ልጆችን ከ18 ዓመት በታች፣ ወጣቶችንና የደከሙ አረጋዊያንን በምስራቅ ሸገር በቦራ ወረዳ ውስጥ በጅምላ አስሮ እያሰቃየ መሆኑን የአከባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ። 

በወረዳው እስር ቤት ውስጥ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ታስረው እየተሰቃዩ ካሉት ኦሮሞዎች የሚከተሉትም እንደሚገኙበት የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል። 

  1. አቶ መልካ ፋጆ ዕድሜ 44 ጅርሜ ቦራ ቀበሌ፣
  2. አቶ ሳዳም ቦኮና ዕድሜ 38 ማሊማ በሪ ቀበሌ፣
  3. አቶ ተረፋ ሚdhaክሶ ዕድሜ 53 ጎራ ለማን ቀበሌ፣
  4. አቶ አባቡ ሚdhaክሶ ዕድሜ 60 ጎራ ለማን ቀበሌ፣
  5. አቶ ነምሶ ፍቃዱ ዕድሜ 32 ኤለን ቀበሌ፣
  6. አቶ ዳሉ በቀላ ዕድሜ 33 ቢቴ Ddhaaባ ቀበሌ፣
  7. የሀገር ሽማግሌ ወይም ሀረጋዊ በቀላ ቡታ ዕድሜ 73 በቴ Dhaaባ ቀበሌ፣
  8. የሀገር ሽማግሌ ወይም ሀረጋዊ ሁሉቃ ለታ ዕድሜ 75 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣
  9. አቶ ገብሬ ናኔሶ ዕድሜ 57 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣
  10. ወጣት ቦቤ ሚdhaክሶ ዕድሜ 20 ባርታ ሳሚ ቀበሌ፣
  11. አቶ ለሚ ሚdhaክሶ ገዳ ዕድሜ 34 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣ 
  12. አቶ ዋሪ ፊታላ ዕድሜ 41 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣
  13. ወጣት አባቡ በdho ዕድሜ 19 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣
  14. ወጣት ቶላ ራባ ዕድሜ 18 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣
  15. ወጣት ገለሼ ኮርቡ ዕድሜ 17 ኤለን ቀበሌ፣
  16. ወጣት ደበሌ በdhoo ዕድሜ 17 ኤለን ቀበሌ፣
  17. አቶ ደነንሶ ተሊላ ዕድሜ 30 ብሾፍቱ ከተማ አስተዳደር፣
  18. አቶ ደጋጋ በdhaadhaa ዕድሜ 53 ጅርሜ ቦራ ቀበሌ፣
  19. አቶ ጨዋቃ ዳdhii ዕድሜ 33 ዳሎታ ማቲ ቀበሌ፣
  20. ወጣት ቶላ ኡርጌሳ ዕድሜ 17 ቂለጡ ኦምቦሌ ቀበሌ፣
  21. ወጣት እንዳላ ሚሊሻ ዕድሜ 19 ቂልጡ ኦምቦሌ ቀበሌ፣
  22. ወጣት ቡኔ ሸንቆ ዕድሜ 22 ቢቴ Dhaaባ ቀበሌ፣
  23. አቶ ቱፋ ኡርጊ ዕድሜ 48 ጅርሜ ቦራ ቀበሌ፣
  24. ወጣት ጁፋራ ደጋጋ ዕድሜ 25 ሁሉቆ ከሺ ቀበሌ እና
  25. ወጣት ኦዳ መልካ ዕድሜ 21 ኤለን ቀበሌ ሲሆኑ፤ 
  26. ወጣት ደናንሶ ገብሬ የሚባል ደግሞ በድብደባ ካደከሙት በኃላ ሞተ ብለው ሜዳ ላይ ጥለውት ከሄዱ በኃላ በህይዎት መትረፉን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በተጨማሪም እነዚህን እስረኞች ከእስር ለማስለቀቅ ወይም ለማስፈታት ገንዘብ ማለትም ከመቶ ሺ እስከ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር እንደሚጠየቁ ቤተሰቦቻቸው ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልፀዋል።

ንፁሃንን እና ኦሮሞነትን በእስር ቤቱ ውስጥ በማሰቃየት ገድሎ ለጅብ በመስጠት የሚፋቅ የመሰለው የፋሽስት አብይ አህመድ የብልፅግና ቡድን የኢምፓየሪትዋን ውድቀት እያፋጠነ ነው።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading