• Sat. Sep 26th, 2026

ኢምፓየርዋ ልትወድቅ በገደል አፋፍ ላይ እያለች የአብይ አህመድ መራሹ ቡድን ከጽንፈኛው የአማራ ፋኖ ጋር በማበር ስልታዊ የስነ ሕዝብ አወቃቀር ለውጦችን ለማድረግ እያሴሩ ነው

Mar 24, 2024

መጋቢት 24/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በምስራቅ ወለጋ ዞን በጎቡ ሰዮ ወረዳ በአሸባሪው እና በሽፍታው የአብይ አህመድ ጦር ሁለት ሰዎች ሲገደሉ፣ በራሱ በአብይ አህመድ ተመልምለው፣ የተደራጁና፣ የታጠቁ የድሮ ስረዓት ናፋቂው የፅንፈኛው የአማራ ፋኖ ቡድን በንፁሃን ህዝብ መካከል ተሰማርተው ሽብርና ማስፈራራትን እንደሚያካሂዱ ለማወቅ ተችሎኣል።

የኦሮሞ ህዝብ በሚያካሄደው የነፃነት ትግል የብዙ ንጹሃን ሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ ነው። ይህም የሆነው የኢትዮጵያ ኢምፖየር እንድትፈርስ የማይፈልጉ ኃይሎች፤ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የጠየቁትን ንፁሃን ዜጎችን ያለ ምንም ጥፋት በጥይት እየቆሉ መፍጀትን ስራዬ ብለው ስለተያያዙት ነው።

በዚሁ መሰረት በምስራቅ ወለጋ በጎቡ ሰዮ ወረዳ ሶሌ ቀበሌ ውስጥ ሰላማዊ ህብረተሰብ ላይ የሰው መብቶች ረገጣ በማከናወን ፈይሳ የተባለዉን ወጣትና ሌላ ስሙ ለጊዜው ያልደረሰን አንድ ሰው በፋሺስቱ የብልፅግና ጦር ተገድለው ሜዳ ላይ እንደተጣሉ ተነግሯል።

በገዢው ስርዓት ካድሬዎች በጎቡ ሰዮ ወረዳ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያሉት ችግሮች በጣም ፍረሃት የፈጠሩ ሲሆን፤ ይባስ ብሎ ይኸው አሸባሪ የብልፅግና ቡድን ለፅንፈኛው የአማራ ቡድን በማገዝ “መልሶ ለማስፈር” በሚል ሰበብ በወረዳው ውስጥ ሰላማዊ ህዝብን እያሰቃዩ እንዳሉም ታውቋል።

እነኚሁ የሚኒልክን ሥርዓት የሚያቀነቅኑ ቡድኖች ባለፉት ወራት “ከጎቡ ሰዮ አከባቢ የተፈናቀሉ ናቸው” ሲባል እንደነበርና በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ መንገዶች በመደራጀት የአከባቢው ሚሊሻ በመምሰል ሰላማዊ ሰዎችን እየገደሉ እና እያስፈራሩ እንዳሉም ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ሰዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል። 

አልገዛም ያለን ሕዝብ ቤቱን፣ እህሉን በማሳ በማቃጠል አና ሃብት ንብረቱን በመዝረፍ፤ በቦታው ደግሞ ያፈናቀለዉን እና የዘረፈዉን ለማስፈር ማኮብከብ ለቅስፈት ይዳርጋል ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading