መጋቢት 26/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኢትዮጵያን ኢምፓየር ለመታደግ እየተውተረተሩ ያሉ ኃይሎች መጋቢት 21/2024 ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሶጌ ወረዳ አዋሳኝ በኩል ወደ ምሥራቅ ወለጋ ሳሲጋ ወረዳ በመግባት ከ100 በላይ የገበሬ ቤቶችን ከሙሉ ንብረት ጋር በእሳት ከማዉደማቸውም በላይ የሰው ሕይወትም መቅጠፋቸዉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጸዋል።
የዚህ ዕኩይ ተግባር አቀነባባሪና አስፈፃሚ የኦሮሚያ ብልፅግና ቡድንሲሆን ‘ከመዋቅሮቻችን ጋር በቅንጅት መስራት’ የሚለዉን መርሆ አንግቦ መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖአል። በዚህም ምክንያት የቤኒሻንጉልጉሙዝን ልዩ ኃይል የኦሮሚያን ድንበር ከፍቶ በማስገባት በዚሁ እለት ከጠዋት ጀምሮ በሳሲጋ ወረዳ በበሬዱ በሎ ቀበሌ ውስጥ እጅግ ዘግናኝ ድርጊቶችን በገበሬዎቻችን ላይ የፈጸሙ ሲሆንቤታቸዉን ከእነ ንብረቱ ከማጋየታቸዉም በላይ ከብቶቻቸዉንም መዝረፋቸው ታውቋል።
እስከ አሁን በአሰቃቂ ሁኔታ ከተገደሉት የአንድ ሰው ስም፣ ከባድ መቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው መሃከል የሶስት ሰዉ ስም እና ቤታቸው እና ንብረታቸው ከወደመባቸው ዉስጥ ደግሞ የስምንት አርሶአደሮችን ስም አግኝተናል። አነርሱም፦
ከተገደሉት፦ ኦቦ ናና ሞሐመድ
ከባድ የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው፦
አብዲሳ፣ ፋጡማ ሞሐመድ እና አብደላ ኡስማን ናቸው።
ቤታቸው ከነንብረቱ የተቃጠለባቸው፦
- ሼክ አቡበከር ከ100 ኩንታል እህል ጋር
- ኦቦ ኢንድሪስ በከሬ ቤታቸው ከነንብረቱ
- ኦቦ ከሊፋ አሊዬ ከ100 ኩንታል እህል እንዲሁም በ100ሺ ብር የሚገመት የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ ሲያጋዩባቸው:
- ሙሳ ኡስማን፣
- አደም ዳካ፣
- ኢብሮ ዩሱፍ፣
- ኦቦ ሚካኤል ኡመሬ እና
- አሂመድ አሊዪ ቤታቸውን ከነንብረቱ አጋይተውባቸዋል ።
በፋሺስት አቢይ የሚመራዉ የብልጽግናው ቡድን ዓላማ ራሱ ያስታጠቃቸውን የጎሮቤት ብሄረሰብ ኃይሎችን ወደ ኦሮሚያ አስገብቶ ሕዝቡን ማስመታት እንዲሁም ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነሠ) ጋር ግንኙነት አላችሁ እያለ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በጅምላ እያሠረ እና በጅምላ እየገደለ ኦሮሙማን ለማጥፋት ነው በማለት ነዋሪዎቹ ለአራታ ቢዮሌሳኦሮሚያ እሮሮዋቸዉን ገልፀዋል።
ይህ ዜና ለኦሮሞ ሕዝብ አንድነት አስፈላጊነት እንዲሁም ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች ደግሞ የገዳይና የአሸባሪ መንግስት ተባባሪ መሆን በታሪክ ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው እንደሚያስገንዘብ ተስፋ አለን።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁ!
