መጋቢት 27/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
አሳውን ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ በሚል መሪ መፈክር የሚንቀሳቀሰው ፋስሽቱ የብልጽግና ስርኣት፣ በምስራቅ አርሲ፣ ዶዶታ ወረዳ፣ በላሌ ቀበሌ፣ ዳሎታ በሚባል ልዩ ሥፍራ 20 የሰላማዊ አርሶ አደር መኖሪያ ቤቶችን ሲያቃጥል ዘጠኝ ነዎሪዎችን ደግሞ አፍኖ የት እንደወሰዳቸው አለመታወቁ ተገልጿል።
የብልጽግናዉ ፋስሽት ሥርኣት ጦር መጋቢት 14/2024 በዚህ በተከበረው የራመዳን ወር ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ስፍራ ላይ ያለ ምንም ምክንያት የሰላማዊ ዜጎችን ንብረት መዝረፍ፣ መኖሪያ ቤቶችንም ከእነ ንብረታቸው ማውደሙም ታውቋል።
በፋስሽቱ ስርኣት ኃይሎች ቤታቸዉ የተቃጠለባቸው ዜጎች ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦
- ሙሳ ካልሎ 1 ቤት፣
- ከሊሎ ኢደ 2 ቤቶች፣
- ጀይሉ ሁሴን 2 ቤቶች፣
- ሃቢብ ሙክታሮ 1 ቤት፣
- አብዱላሂ አብደላ 3 ቤቶች፣
- አብዱሌ ቱጃራ 1 ቤት፣
- ሱልጣን ቱጃራ 1 ቤት፣
- ጣሃ ሙሐመድ 2 ቤቶች፣
- ፋዮ ጋና 2 ቤቶች፣
- ሱልጣን ቶሎላ 2 ቤቶች፣
- ኡርጌሳ ድሃቃቦ፣ 2 ቤቶች እና
- ጣሃ ሙሐመድ 1 ቤት መሆናቸው ሲታወቅ፣
ታፍነው ወዴት እንደተወሰዱ ያልታወቀዉ ዜጎች ዝርዝር ፦
- ካልሎ ኢዶ፣
- ካቦ ዳሩ፣
- አብሹ መሁመድ፣
- ጣሁ ጎልብቻ፣
- ቃዲ አህመድ፣
- ጣሁ አሳባን፣
- ሁሴን መሃመድ፣
- አብዲ አህመድ እና
- አብደላ ፋኖ የተባሉት ነዋሪዎች ናቸው።
የብልጽግና ሥርኣት ዶዶታ ወረዳን ጨምሮ፣ በተለያዩ የዞኑ ወረዳዎች ውስጥ ግዲያ፣ ዝርፊያዎችን እና የነዋሪዎችን መኖሪያ ቤቶች እያቃጠለ መሆኑን አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከምንጮቹ ማረጋገጥ ችሏል።
የንጹሃን ኦሮሞዎችን ቤት ማቃጠል፣ አስሮ ማሰቃየትም ሆነ አፍኖ መውሰድ የነፃነት ትግሉን ወደ ኋላ እንደማይመልሰዉ ጠላትም ሆነ ወዳጅ ሊገነዘበው ይገባል።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
