• Sat. Sep 26th, 2026

የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምዕራብ ሸገር አደአ በርጋ ወረዳ ውስጥ በወሰደው እርምጃ አንድ ሬጂሜንት የጠላት ኃይልን አይቀጡት ቅጣት ሰጥቶአል

Mar 28, 2024

መጋቢት 28/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ክንድ እና ጋሻ የሆነው የመካከለኛው ዞን የኦሮሞ ነፃት ሰራዊት በፋሽስቱ የብልፅግና ጦር ላይ መጋቢት 19/2024 በምዕራብ ሸገር ዞን አደአ በርጋ አከባቢ በሞገር ከተማ አቅራቢያ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ በወሰደው እርምጃ አንድ ሬጂሜንት የጠላት ኃይልን ሙሉ በሙሉ ደምስሷል።

በዚህ አመርቂ እርምጃ የጠላት ጦር ታጥቆ የተሰማራውን መሳርያ አንድ ሞርታር፤ አንድ ዲሽቃ፤ አስር ብሬኖችን፤ ስድስት ሰናይፐሮችን እና ኤኬኤም (AKM) መሉ በሙሉ ከላያቸው ላይ በመፈታት ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርጓል።

ከ110 በላይ የሚሆኑ የብልፅግና ወታደሮችንም ማርኮ አስፈላጊውን ጥበቃ እያደረገላቸው መሆኑንም ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በማሳወቅ የኦሮሞ ህዝብን እንኳን ደስ አላችሁ አንኳን ደስ አለን ብሏል።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading