መጋቢት 31/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ህዝቡን በፍርሃት ሸብቦ ለመግዛት የአገዛዝ ዘዴውን እያስተካከለ ያለዉ የፋሺስቱ ብልጽግና ቡድን፣ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የህብረተሰቡን ንብረትና መኖሪያ ቤቶች በእሳት ማውደሙን ቀጥሏል።
በዚሁ መሰረት፣ መጋቢት 17/2024 በምስራቅ ሸገር ዞን፣ ቦሰት ወረዳ፣ ሲፋ ባቴ ቀበሌ ውስጥየተሰማሩት የኢምፓየሪትዋ ታጣቂዎች የነዋሪዎችን በርካታ ቤቶች በእሳት ማውደማቸውን አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከምንጮቹ ማረጋገጥ ችሏል።
እድሜአቸውን ሙሉ ያፈሩትን ሃብት እና ንብረት ከመኖሪያ ቤቶቻቸው ጋር በእሳት የወደመባቸው ነዋሪዎች ቁጥር በርካታ ነው። ከእነዚህም ለጊዜው ስማቸው የደረሱን ተጎጅዎች፦
- ገለቲ ቱማ፣
- ገቦ ገለቲ፣
- ቦርሳ ገለቲ፣
- ሁሴን ዳሌ፣
- ተሰማ ሰንበቱ፣
- አሰፋ ሰንባቱ፣
- ሹራ ጀዶ፣
- ጁንዲ አብቲ፣
- ሁሴን ገለቲ፣
- ደልቡ አቢቲ፣
- ከሊሎ አማኖ፣
- አዴዴ አሹ ሃጂ ሃቆ፣
- ሂርኮ ሆርዶፋ እና
- ደቻሳ ቡኔ ናቸው።
የፋሺስት አቢይ የማቃጠል እና የዝርፊያ ቡድኑ ከዚህ በላይ ስማቸዉ የተጠቀሱት ሰላማዊ ሰዎች እህልና የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች ጭምር ከማዉደማቸዉም በላይ የነበሩዋቸዉን ፍዬሎችና በጎችን የቻሉትን አርደዉ ከመብላትም አልፈው የተረፋቸዉን ደግሞ ዘርፈዉ መሄዳቸዉም ተገልጿል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦ “የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
