• Tue. Sep 1st, 2026

የኢምፓየሪትዋን መከላከያ ሰራዊት በመክዳት ሁለት አባላቱ በምስራቅ ወለጋ ዞን ሲቡ ሲሬ ወረዳ ዉስጥ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ዉስጥ መቀላቀላቸው ተነገረ

Mar 31, 2024

መጋቢት 31/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ህዝባቸውን ለመዉጋት በፋሺስቱ የብልጽግና ሰራዊት ዉስጥ ተቀላቅለው ሲያገለግሉ የነበሩ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስርኣቱን በመክዳት በምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ሲቡ ሲሬ ወረዳ በቡጁራ ከተማ ከሚኘዉ ካምፕ በማምለጥ፤ መጋቢት 18/2024 በዚሁ ወረዳ ወስጥ ወደ ሚንቀሳቀሰው ጀግናው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በመሄድ መቀላቀላቸውን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ምንጭ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግሮዋል።

በዚሁም አንድ ስናይፕር፣ አንድ የቱርክ AKM፣ 465 ጥይቶች እና ሁለት የእጅ ቦምቦች እንዲሁም አምስት ሳጥን ጥይት ከካምፑ ያወጡትን ለትግሉ ገቢ አድርገዋል።

ወደ ህዝባቸው ትግል ለተቀላቀሉት ለእነዚህ አባላት በኦሮሞ ነፃነት በኩል ሞቅ ያለ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፣ የቀሩት ሌሎች የኢምፓየሪትዋ መከላከያ አባላትም ከእነዚህ ቆራጥ ወታደሮች በመማር እና ፈለጋቸውን በመከተል ወደ ህዝባቸው ትግል እንዲቀላቀሉ ጥሪ መደረጉ ታውቋል።

የኢምፓየሪትዋ መፈራረስ ምልክቶች ከሆኑት ዉስጥ አንደኛው እና ወሳኙ ምልክት ዘቡ እራሱ በእምቢተኝነት ከድቶት መዉጣቱ ነው። ይኸውም የኦሮሞ ሕዝብ ለኢምፓየርዋ ላለመገዛት እምቢተኝነቱ እና እንድነቱን የሚያመላክት እንደሆነ ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል።

ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading