መጋቢት 31/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የአብይ አህመድ ብልፅግና አገዛዝ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለዉ መከራና ስቃይ ቀደም ሲል ከነበሩት የጉልበተኛ መንግሥታት አገዛዝ በእጥፍ የከፋ ስለመህኑ ድርጊቶቹ ጠቋሚዎች ናቸው።
በርካታ ንጹሃን ኦሮሞዎችን ፍርድ ቤት ሳያቀርቡ በድብቅ እሥር ቤቶች ውስጥ ከማሰቃየት አልፎ መግደል ስርዓቱ ምን ያህል ኢፍትሃዊ እንደሆነ በግልጽ ያመለክታል።
ይህ ህዝባዊ መሰረትና ቅቡልነት እጦት ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ውስጥ የተዘፈቀው በፋሽስቱ አብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ቡድን፣ በምዕራብ ሸገር ዞን፣ ከአምቦ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌዎች ሰላማዊ ነዋሪዎችን እያጋዘ ወደ ዞኑ ከተማ አምቦ በመውሰድ በድብቅ እስር ቤቶች ዉስጥ እንደሚያሰቃይ ታዛቢዎች በሰፊው ያናገራሉ።
በዚህም መሰረት በኮሎኔል አቢይ አህመድ የሚመራው የኢምፓየሪቱ ጦር መጋቢት 16/2024 ለዚሁ ለፋሺስቱ ስርኣት ድርጊት ሰለባ የሆኑ ከተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ከያዝዋቸዉ ሰዎች መሃከል አስራ አራቱን በከተማው በሚገኘው ጸረ ሽምቅ ውጊያ በሚባለዉ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ በማሰር እያሰቃዩዋቸዉ መሆኑን የአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ምንጮች ገልጸዋል።
ከታሰሩት14 ሰዎች መካከል ለጊዜው ስማቸውን ያገኘነው፦
- አለሙ ተሬሳ የቤተሰብ ሃላፊ፣
- ዲንገታ አሌ፣
- ተመስገን ሽብሩ፣
- ዮኔ ካፍታሙ፣
- ትግስቴ ሽብሩ እና
- ካሪም ሺፈራ ናቸው።
ታሳሪዎቹ በየምሽቱ ለከፍተኛ ድብደባ ስለሚጋለጡ እና በድብደባዉም ወቅት ከፍተኛ ጩኸት ስለሚያሰሙ የአካባቢዉ ሕዝብ በጭንቀት ዉስጥ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም
