ሚያዚያ 1/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በኮሎኔል አብይ ኣህመድ ትእዛዝ የተሰማራው የኣገዛዙ ታጣቂዎች በምእራብ ሸገር በዳንዲ ወረዳ ወደ ሰላማዊ ነዋሪዎች መንደር በመሰማራት ለሁለት ቀናት የነዋሪዎችን ቤቶች ሲያቃጥሉ ቆይቶአል።
በዚሁ መሰረት መጋቢት 12/2024 በምእራብ ሸገር ዞን ዳንዲ ወረዳ ዳኒሳ ሾኖ ቀበሌ ውስጥ የኢምፓየሯ ታጣቂዎች የሁለት ገበሬዎችን ቤቶች ከነንብረታቸው ማቃጠላችውን ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጸዋል።
ቤቶቻቸው የተቃጠለባቸው ሰዎችም ኮርሜ ወርቁ እና ተሩ ኡርጌሳ ሲሆኑ፣ በግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው እራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ አርሶ አደሮች እንጂ፣ በፖለቲካ ዉስጥ ምንም ሚና እንደሌላቸው ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ኦሮሞን ቤትና ንብረት አልባ በማድረግ በዚህ ዓመት ብቻ በ100 ሺ የሚቆጠር ሕዝባችን የሰው እጅ እንዲያይ እየተገደደ ነው።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
