ሚያዚያ 1/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የአሸባሪውን አብይ አህመድን ዕቅድ እና ዓለማ ለማሳካት ፀረ-ሕዝብ ስልጠና ተሰጥቶት የተሰማራው እና ይህንን ስራውን ዕለት ተዕለት እየሰራ የሚውለው የአትዮጵያ ኢምፖየር የመከላከያ ሰራዊት ተብዬዉ ሽፍታ ነብስ-በላ ሰራዊት በንፁሃን እና ሰላማዊ ህዝብ ላይ የሚያደርገውን አሰቃቂ ግድያ አጠናክሮ በመቀጠል በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ቤትን እና ቀዬ በሀዘን እያጥለቀለቀው ይገኛል።
በዚሁ መሰረት መጋቢት 20/2024 በምዕራብ ሸገር፣ በጀልዱ ወረዳ፣ ጫንጮ ቀበሌ፣ ኦቦ አያና ሲወያ የተባሉ የአምስት ቤተሰብ አባት የሆኑ ግለሰብ፣ ከአብይ አህመድ ቀኝ እጅ፣ ከሺመልስ አብዲሳ የግደል ትዕዛዝ ተቀብሎ በተሰማራው ጦር በሌሊት ስድስት ሰዓት ገደማ ቤታቸው ዉስጥ በጥይት ኡሩምታ መገደላቸውን የቤተሰቡ አባላት ተናግረዋል።
ኦቦ አያና ሲወያ የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸውና በግብርና ስራ ተሰማርተዉ ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ሰው ሲሆኑ፤ ይኸው ለግድያ የተሰማራው የጦር ቡድንም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትቀልባለህ በሚል የሃሰት ወንጀል እንደገደሏቸውም ታውቋል።
በዚህ ወረዳ ውስጥ ከግድያ በተጨማሪ ለአንድ ሳምንት በተከታታይ ቀናት የማያቋርጥ ዝርፊያ እና እስር በዚሁ ጦር ቡድን እየተካሄደ ሲሆን፣ በDhሃስ ቆርቻ ቀበሌ ውስጥ የቤተሰብ ሃላፊ የሆኑ ኦቦ ሶሪ አበራ ፈይሳ የተባሉ ግለሰብን መገደላቸውን ከዚህ በፊት ዘግበን ነበር።
የንጹሃን ኦሮሞዎችን ህይወት መቅሰፍ እና ሃብትንብረታቸውን መዝረፍ የነፃነት ትግሉን ወደ ኋላ እንደማይመልሰዉ ጠላትም ሆነ ወዳጅ ሊገነዘበው ይገባል።
ከወሎ ሕዝባችን ጎን በአንድነት እንቁም!
