• Tue. Nov 24th, 2026

“ኦሮሞን እንደ ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በኢኮኖሚ ኋላ ቀር ማድረግ የመጀመሪያው አላማዬ ነው።” ብሎ የተነሳ የሚመስለው የኢምፓየሪቱመሪ አቢይ አህመድ በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ የአርሶ አድር ቤት እና ንብረት እንዲያቃጥሉ ቡድኑን አሰማርቶአል

Apr 4, 2024

ሚያዚያ 4/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የከፋ ጭቆናና ክፋት በኦሮሞ ህዝብ ላይ እያካሄደ የሚገኘው የኮሎኔል አብይ አህመድ ቡድን ወደ ሥልጣን ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው ይህ ነው የማይባል ግፍ እንዲሁም፤ ኦሮሞን እንደ ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በኢኮኖሚ ኋላ ቀር ማድረግን የመጀመሪያ አላማው አድርጎ የተነሳ  የሚመስለዉ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የኢምፓየሪቱመሪ የሰላማዊ ኦሮሞዎችን ቤት ከእነ ንብረቱ በማቃጠል እና በመዝረፍ ህዝባችንን በስጋት ውስጥ እየጣለው ነው።

ይኸውም መጋቢት 26/2024 በምዕራብ ወለጋዞን ቤጊ ወረዳ ጢሎ ቀበሌ ነቃ ፈርዳ በተባለ ሥፍራ የኢምፓየርዋን ሰራዊት በማሰማራት  የሰብል ምርትና የቤት ንብረት የዘረፉ ሲሆን ማጓጓዝ የቻሉትን ንብረትና ከጎተራ ያለ እህል ጭምር ከነቤቱ በእሳት አዉድመዋል።

ንብረታቸው የተዘረፉና እህላቸው ከተቃጠለባቸው መሃከል ስማቸውን ለጊዜው ያገኘነው፦

  1. ያሲን በለጣ ሹሬ 22 ኩንታል የተለያየ የእህል ዘርእቤቱ ውስጥ የነበረ ዕቃን ጨምሮ ተዘርፎዋል፣
  2. አቡሉ አሊ ለሙ 23 ኩንታል እህል ከሙሉ የቤትዕቃ ጋር ተዘርፎዋል፣
  3. ከማል ወንድሙ ለሙ 10 ኩንታል እህል ተዘርፎዋል፣
  4. ኪበቡ ጀርፉ ሞሳ ቤት ከነንብረቱ አቃጥለውበታል፣
  5. ጂባ ሰንበቶ ቤትና፣ ቤት ዉስጥ ያለውን ንብረቱንና እህል አብረው አቃጥለዋል፣
  6. ዳዊት ታፈሳ ተሊላ ቤትና፣ ቤት ዉስጥ ያለውን ንብረቱንና እህል አቃጥለዋል፣
  7. ገመቹ አያና ቤት፣ ቤት ዉስጥ ያለውን ንብረቱንና እህል አቃጥለዋል።

ይህንንም የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

ይህ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የተፈጸመባቸው  ግለሰቦች በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ ሰላማዊ ሰዎች ሲሆኑ ሃብት ንብረታቸውን ለመዘረፍ እና በእሳት ለማዉደም ያበቃቸው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ የሚል የሃሰት ዉንጀላ እንደሆነ የአካባቢዉ ነዋሪዎች አክለው ገልጸዉልናል።

አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply