• Wed. Nov 25th, 2026

የኦሮሞ ህዝብን ከምድረገጽ የማጥፋት ዓላማው አድርጎ የተነሳው ፋሺስት አብይ አህመድ የብልፅግና ታጣቂ ቡድኑን በመጠቀም በምሥራቅ ሸገር ዞን ዱግዳ ወረዳ የንጹሃንን ንብረት በማጋየት ለስደት እየዳረጋቸው ይገኛል

Apr 5, 2024

ሚያዚያ 5/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብን ከምድረገጽ የማጥፋት ዓላማቸው አድርገው እንዲሰሩ ስልጠና የተሰጣቸው የብልፅግናው ታጣቂ ቡድኖች በአሁኑ ሰዓት በመላው ኦሮሚያ ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ ግለሰቦችን ከመግደል አልፎ ቤታቸውን ከእነ ንብረቱ በማጋየት ለስደት እየዳረጉዋቸው ይገኛሉ።

መጋቢት 23/2024 በምሥራቅ ሸገር ዞን ዱግዳ ወረዳ ቢርቢርሳ ጉዳ ሰቦሌ ቀበሌ ውስጥ ለጥፋት የተሠማሩት ወታደሮች የሶስት ገበሬዎችን ቤት ከነንብረቱ እንዳጋዩት የአከባቢው ነዋሪዎች ለአራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።

ቤታቸው የተቃጠለባቸው ገበሬዎች መሆናቸው ሲታወቅ ስማቸውም፦ 

  1. ኦቦ ኢፋ ቢራኑ፣ 
  2. ኦቦ ቃጫ አያኖ እና 
  3. ኦቦ ኢፍታሁ ኮርቡ ይባላል።

እነዚህ ቤታቸው የተቃጠለባቸው ሰዎች በእርሻ ስራ ተሰማርተው ቤተሰቦቻቸውን ከማስተዳደር ውጪ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ሚና እንደሌላቸዉ ምንጮቻችን ይናገራሉ። ሆኖም ግን በዕድሜም እንኳን የገፉ ሲሆኑ ያለምንም ማስረጃ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ትቀልባላችሁ በሚል የሃሰት ዉንጀላ ቤቶቻቸው እንደተቃጠለባቸው ምንጮቻችን አክለው ገልፀውልናል።

አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ በመሆኑ ነው።”

Leave a Reply