• Wed. Nov 25th, 2026

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ ውስጥ ውጪ ሐገር ትሄዳላችሁ በማለት ወጣቶችን አታልለው እየመዘገቡ እንደሆነ ታውቋል

Apr 6, 2024

ሚያዚያ 6/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በተለምዶ መድህን ተብሎ በሚጠራ አከባቢ የፋሺስቱ አብይ አመራር ወደ ውጪ ሐገር በብልጽግና ፈቃድ ትሄዳላችሁ በማለት ወጣቶችን እየመዘገቡ እንደሚገኙ ታውቋል።

ለዚህ ምዝገባም ከመቶ ተመዝጋቢዎች 75ቱ ወንዶች እንደሚፈለጉና ለምዝገባም 150 ብር እየከፈሉ እንደሚመዘገቡም ተገልጿል። ምዝገባዉንም እዉነት ለማስመሰል አንዳንድ ወጣቶች ነቀምቴ ሄደው ፊርማቸውን ፈርመው ደረሰኝ እንዲቀበሉ አድርገዋል። ሆኖም ደረሰኙም ውሸት መሆኑና ወጣቱን ለማሞኘት የተደረገ እንደሆነ ታውቋል።

ለተባለው ጉዞ ዝግጁ ለማድረግም የብቃት ስልጠና ፊንፊኔ ዉስጥ እንደሚሰጣቸውም ጭምር ተነግሮዋቸዋል።

ወደ ውጪ ሐገር ትሄዳላችሁ በሚል ሰበብ የተመዘገቡትን ወጣት ወንዶች በአውሮፕላን ወደ አረብ ሐገር ተልከዋል። ለወደፊትም ወደ ካናዳ ትሄዳላችሁ ተብለው የተመዘገቡትን ወደ አረብ ሐገር ፋሺስቱ አብይ አህመድ ሊልካቸው  አንደተዘጋጀ ዉስጥ አዋቂዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጸዋል።  

ከተመዘገቡት ከፊሎቹን ደግሞ ወደ ወታደራዊ ማሠልጠኛዎቹ እያስገባቸዉ መሆኑም ታውቆዋል።

የብልፅግናው ፋሺስት አንጃ አሁን እየታየ ያለው የስራ አጥረትን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል እያሳየ ነው።

በተጨማሪም በዚሁ በጊምቢ ከተማ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሰርቲፊኬት የያዙትንና  ስምንተኛ ክፍልን ያጠናቀቁ  ወጣቶች አየተመዘገቡ መሆኑ  ታውቋል።

ምዕራብ ወለጋ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎች ብቻ እስከ አሁን ከ3000 በላይ ወጣቶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ጊምቢ ድረስ ሄደው መመዝገባቸውን አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ከምንጮቹ መረጃ አግኝቶዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ የኦሮሞን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ የጦር ሜዳዉ እራት ማድረግ ከጀመረ ቢቆይም ዛሬ ከዚያም አልፎ ደግሞ ወንድ ወንዱን ለባርነት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለዚያውም በዉዴታ ወደ አረብ ሐገር እየላከ እንዳለ ከዚህ በላይ ማስረጃ አይኖርምና በጊዜ ይህንን ፋሺስት ማስወገድ ይገባል።

Leave a Reply