ሚያዚያ 6/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የማፍያ ሰራዊቱ ግፍና በደል በኦሮሚያ ጎልቶ እየወጣ ነው። በአሁኑ ወቅት ሰላማዊው የኦሮሞ ማህበረሰብ በአብይ አህመድ ብልፅግና አምባገነናዊ አገዛዝ ሰራዊት በመላው ኦሮሚያ እየተጨፈጨፈ ይገኛል።
መጋቢት 13/2024 በኢሉ አባ ቦራ ዞን ዳሪሙ ወረዳ ሜጢ ቀበሌ ዉስጥ ሁለት ሰላማዊ ሰዎች በአምባገነናዊዉ አብይ አህመድ አገዛዝ ሰራዊት መገደላቸዉ የተነገረ ሲሆን፣ የተገደሉት ሰዎች ስማቸው ኦቦ ጢላሁን ሃምባ እና ኦቦ ታጁ ተማም የተባሉ እንደሆነ ታዉቋል።
እነኚህ ገዳይ ሰራዊት ወደ ኦቦ ታጁ ተማም ቤት በሄዱበት ወቅት ኦቦ ጥላሁንም እዛው ስለነበሩ እናንተ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት ኣላችሁ በማለት ሁለቱንም በጥይት ደብድበው እንደገደሏቸው ምንጮቻችን ገልጸዉልናል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ ምንም አይነት ህክምና እንዳያገኙ ትዕዛዝ የሚሰጥ ኢ-ሰብዓዊነትን የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
