ሚያዚያ 7/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሞን ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ሕዝቡን መግደል እንደ ግዴታው አድርጎ በፋሺስት አቢይ ጠንሳሽነት በህቡዕ የተደራጀው “የሰላም ኮሚቴ” ብሎ እራሱን የሚጠራው ህቡዕ ገዳይ ቡድን በሺመልስ አብዲሳ አመራርና ትዕዛዝ ሰጪነት እየተመራ በመላው ኦሮሚያ አሠቃቂ ግድያዎችን መፈጸሙን ቀጥሏል።
በዚህም መሠረት የብልፅግናው ጦር ገዳይ ቡድን መጋቢት 28/2024 በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ጩቃላ ወረዳ የ80 ዓመት አዛውንቱን ኦቦ ሲዳ ተሊላን ቤታቸው ድረስ በመሄድ በቤተሰቦቻቸው ፊት ጥይት አርከፍክፈዉ ገድለዋቸው መሄዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
አቦ ሲዳ ተሊላ በተለያየ ጊዜ ልጅዎት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባል ነው በማለት ሲታሠሩም ሲፈቱም ነበር። እነዚሁ የጥፋት ቡድኖች ከአመት በፊት ቤታቸውን ከእነ ሙሉ ንብረታቸው አቃጥለውባቸውም ነበር።
እኚህ የ80 ዓመት አዛውንት በዚህ እድሜያቸው በፖለቲካ ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ እንዳልነበራቸው ቢታወቅም፤ ልጃቸው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ዉስጥ መቀላቀል እና በፋሺስት አልመራም ማለት የሊበን ጩቃላ ወረዳ አስተዳደርን እንቅልፍ ነስቶት ነበር። በዚህም መሰረት የወረዳው አስተዳዳሪ ደበሌ ነጉ የተባለው ገዳይ ጦሩን ይዞ ወደ ቀዬአቸው አገምሳ ሮጊቻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎሮ ወደ ተባለ ቦታ በመሄድ እንደገደሏቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጸዋል።
ይኸዉ የሰላም ኮሚቴ ብሎ የሚጠራው የገዳይ ቡድን ባለፈው ሕዝቡን ስብሰባ ጠርተው፣ የጠረጠርነውን ሁሉ እንድንገድል ትዕዛዝ ስለተሰጠን እኛ እንደምንላችሁ የማትኖሩ ከሆነ እንጨርሳችኋለን በማለት ሕዝቡን ሲያስፈራሩ እንደነበረ መዘገባችን አይዘነጋም።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የአውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”






