• Tue. Nov 24th, 2026

የክፉኝ በሽታ በሰሜን እና በምዕራብ ሸገር ዞኖች ውስጥ ሰው መግደል ጀምሯል

Apr 7, 2024

ሚያዚያ 7/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የማፍያው የብልጽግና ቡድን የኦሮሞ ህዝብ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ እና የመድኃኒት እጥረትንም መፍጠር በክልሉ ዉስጥ እንዲከሰት ስልታዊ አካሄድ ከጀመረ አመታትን አስቆጥሮዋል። በዚህም ምክንያት የመንግሥት አገልግሎትን እንደ ጦር መሳሪያ መጠቀም በመጀመሩ የወረርሽኝ በሽታዎች ህብረተሰቡን እየገደሉት ይጉኛሉ።

በዚህ መሠረት በሰሜን ሸገር ዞን በበርካታ ወረዳዎች የክፉኝ ወረርሽኝ በመታየቱ በሕዝቡ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን እያስከተለ ነው። በሰሜን ሸገር ዞን እንደ ኩዩ፣ ወረ ጃርሶ፣ ሂDhaቡ አቦቴ እናደገም ወረዳዎች እንዲሁም በምዕራብ ሸገር ዞንደግሞ እንደ ግንደበረት፣ አድአ በርጋ እና ሜታ ወልቂጤ ወረዳዎች የህፃናትንና የወጣቶችን ሕይወት መቅጠፍ ከጀመረ ዉሎ አድሮል።

በሰሜን ሸገር ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ብቻ እሰከ መጋቢት 18/2024 ድረስ የ14 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።

ይህ በሽታ ተላላፊ ከመሆኑም በላይ በሽታዉም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚገል ነዉ። ይኸውም በቂ ህክምና እና ጊዜውን የጠበቀ ክትባት ለህበረተሰቡ ባለመሰጠቱ የሚከሰት በሽታ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

ይህም የፋሺስቱ አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን የኢምፓየሪትዋን የፖለቲካ ሥልጣን ከያዘ በኋላእና በኦሮሚያ ላይ ጦርነት ካወጀበት ጊዜ ጀምሮበገጠርና ትናንሽ ከተሞች ውስጥ እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በስፋት ይንቀሳቀስባቸዋል ያላቸውን ዞኖች በሙሉ መድኃኒት ማቋረጥና የባለሞያ እጥረት በመፍጠር ችግሩ እንዲባባስ ማድረጉን ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።

በሰሜን ሸገር ወረ ጃርሶ ወረዳ ፋጂ ኤጄርሳ ቀበሌ ውስጥ ብቻ በዚህ በሽታ ከሞቱት 10 ህፃናት 3 ወጣቶችና አንድ አዋቂ ሲገኙበት ስማቸዉ እንደሚከተለው ነው፣

  1. ኢሜ ቦጁ ቱሉ ዕድሜ 2፣
  2. አብዲ አዳሙ አባጣ ዕድሜ 2፣
  3. ኢሜ ቀኒዬ ደሶሉ ዕድሜ 2፣
  4. ሎሚ ቶለሳ አሰፋ ዕድሜ 2፣
  5. ኦብሴ ጎቡ ፈዪኔ ዕድሜ 3፣
  6. ለሚ ጀባኑ ባቢሌ ዕድሜ 3፣
  7. Dhiሬ ተጀቤ ጢቤ ዕድሜ 4፣
  8. ሰበቱ ኢጃራ ባዪሳ ዕድሜ 4፣
  9. ዲሪቤ Dhuጋሳ ጆቢሩ ዕድሜ 4፣
  10. ሀጫሉ ቡልቱሜ ቡልቶ ዕድሜ 11፣
  11. አስቴር ግርማ ዕድሜ 12፣
  12. አበቡ ተገኑ ገመዳ ዕድሜ 12፣
  13. ኢረና ኑጉሤ ጀቤሳ ዕድሜ 18 እና
  14. ባጫ መርጌ ዕድሜ 45

መሆናቸው ታውቋል።

የክፉኝ ወረርሽኝ በምሥራቅ ሽገር ዞን ዱግዳ ወረዳ እና ቦራ ወረዳ እየተስፋፋና ህዝቡ ለህክም እየተቸገረ መሆኑን መዘገባችን አይዘነጋም።

“አሳውን ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ” በሚል መሪ መፈክር የሚንቀሳቀሰው የፋስሽቱ አብይ አህመድ መራሹ ቡድን ከዚህ በላይ የጦር ወንጀል ሊፈጽም አይግባዉምና ሕዝባችን በአንድነት ተነስቶ ይህንን ስርዓት መገርሰስ አለበት። በኢምፓየሪትዋ ዉስጥ የምትኖሩ ጭቁን ሕዝቦች ፋሺስት አቢይ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚያደርገዉ የጦር ወንጀል ‘ነግ በእኔ’ ብላችሁ እንድታስቡም እናሳስባለን።

Leave a Reply