ሚያዚያ 7/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት የሰፊውን ህዝብ አደራ ከተረከበበት ዕለት ጀምሮ ከቤቱ የወጣለትን አላማ አንግቦ ያለ ዕረፍት ቀንና ሌሊት ደከመኝ፣ ራበኝ፣ ተቸገርኩ፣ ሰለቸኝ ሳይል፣ ሀሩር፣ ብርድና ዝናብ እየተፈራረቁበት ከህዝቡ ትከሻ ላይ የጭቆናን ቀንበር ለማንሳት የጠላቱን ጉሮሮ በማነቅ አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ታላላቅ ድሎችን ማስመዝገቡን ቀጥሎበታል።
በዚሁ መሠረት መጋቢት 28/2024 በምዕራብ ሸገር ዞን ጮቢ ወረዳ በጉቶ ከተማ እና በከተማው አስተዳደር ስር በሚገኙ አራት የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ አዱ ሳፋ ብርጌድ በወሰደው ከባድእርምጃ የፋሺስት አብይን ሰራዊትን አራውጦ መግቢያ በማሳጣት ከመማረክም በላይ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን በማስፈታት ለነፃነት ትግሉ ገቢ አድርጎዋል።
በዚህ የማጥቃት ጦርነትም 26 የፋሽስቱን ሰራዊት በሞት ሲቀጣ፣ 42ቱን ክፉኛ አቁስሎ፣ 17ቱን ደግሞ ከሙሉ ትጥቃቸው ጋር ማርኳል። በዚሁም አኩሪ ድል ማስመዝገቡን ገልጿል።
በዚህ ድልም በመሣሪያ በኩል 53 AKM ከነሙሉ ትጥቁ፣ 2 ስናይፐር፣ 3 ጊርኖፋ ቱቦዎችከዲሽቃ ጥይቶች ጋር፣ ጊርኖፋ እና ሌሎች የተለያዩ መሳሪያዎች ለኦሮሞ ነፃነት ትግል ገቢ አድርገዋል።
ድል ለተጨቆነው የኦሮሞ ሕዝብ ተመኘን!
