• Tue. Nov 24th, 2026

በምስራቅ ሸገር ዞን በዱግዳ ወረዳ ውስጥ የአርሶ አደሮች ቤት በፋሺስት አብይ አህመድ ጦር ቡድን በመቃጠሉ ወድመዋል

Apr 20, 2024

ሚያዚያ 17/2024 አራታ ቢዮሌሰ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብን ከምድረ፡ገፅ የማጥፋት እቅድ አቅደው እየሰሩ ያሉት የማፍያው የብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ውስጥ በአሳቃቂ ሁኔታ ከፖለቲካ ነፃ የሆኑ ንፁሃን እና ሰላማዊ ሰዎችን ከመግደል አልፈው ቤቶቻቸውን ከቤት  እቃዎቻቸው ጭምር በማቃጠል ለስደት እየዳረጉዋቸው ነው።

መጋቢት 23/2024 በምስራቅ ሸገር ዞን በዱግዳ ወረዳ ቢርቢርሳ ጉዳ ሰቦሌ በሚባል ቀበሌ ውስጥ እነዚህ ለጥፋት የተሰማሩ የብልፅግና ሠራዊት አባላት የሶስት አርሶ አደር ቤቶችን ከነንብረታቸው በእሳት ማውደማቸውን ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ነግረዋል።

እነዚህ ቤቶቻቸው የተቃጠሉባቸው ሰዎች ስም፦

  1. ኦቦ ኢፋ ብረሃኑ፣
  2. ኦቦ ቀቻ አያኖ እና
  3. ኦቦ ኢፍተሁ ኮርቡ የተባሉ ናቸው።

እነዚህ ቤቶቻቸው የተቃጠለባቸው ሰዎች አርሶ አደሮች ሲሆኑ በግብርና ስራ እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን የሚያኖሩ እና የፖለቲካ የተሳትፎ የሌላቸው ሰዎች መሆናቸውንም ነዋሪዎች ተናግረዋል።

እንዲሁም እነዚህ ሰዎች በዕድሜ የገፉ ሰዎች ሲሆኑ በሃሰት ዉንጀላም፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ትቀልባላችሁ ብለው ቤታቸውን እንዳቃጠሉባቸው ነዋሪዎች ጨምረው ገልፀዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply