• Tue. Nov 24th, 2026

ጀግናዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ አርሲ፣ ዞን መርቲ ወረዳ፣ የኢምፓየሪቱን ወራሪ ሰራዊት በመግደልና በማቁሰል  መቅጣቱን ገለጸ

Apr 20, 2024

ሚያዚያ 17/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ጋሻና መከታ የሆነዉ ጀግናዉ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በምስራቅ አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ ዋታሮ ዲኖ ቀበሌ ልዩ ስሙ Dhaባማ በሚባል ስፍራ የጠላትን ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ አድርጓል።

መጋቢት 29/2024 ጀግኖቹ የህዝብ ልጆች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሃምባ አኖሌ ብርጌድ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እንቅስቃሴ ፍተሻ በሚል ዘመቻ ተንቀሳቅሶ የህዝባችንን ቤት፣ ከብት፣ ግመልና ሌሎች ንብረቶችንም በእሳት በማጋየት ላይ የነበረዉ ወራሪ ሰራዊት ላይ በደፈጣ በሰነዘረዉ ጥቃት ከጠላት ሰራዊት አስሩን ሲገድል ሃያ ሁለቱን ደግሞ በማቁሰል የጠላት ጦርን እንቅስቃሴ አጨናግፏል።

ጀግናዉ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በወራሪዉ የኢምፓየሪቱ ሰራዊት ላይ እየወሰደ ያለዉ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል።  

ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!

Leave a Reply