ሚያዚያ 20/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ላለፋት ስድስት ዓመታት የኦሮሞ ህዝብን እረፍት የነሱት የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ታጣቂ ቡድን መሆናቸዉን ስንዘግብ ቆይተናል። እነርሱም በሚንቀሳቀሱበት ቦታዎች ሁሉ መደበኛ ስራቸውን እያከናወኑ ያሉትን ሰላማዊ የኦሮሞ ህዝብን በሃሰት ዉንጀላ ማለትም የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትቀልባላችሁ እንዲሁም ትደግፋላችሁ በሚል ስም ያለምንም ርህራሄ የጥይት እራት አድርገው እየገድሉ፣ ማጓጓዝ የሚችሉትን ንብረታቸውን በመዝረፍ፣ መዝረፍ ያልቻሉትን ደግሞ የመኖሪያ ቤታቸውን ጨምሮ በእሳት እያወደሙ ይገኛሉ። በዚህም ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ የመኖር ህልውና ለአደጋ እያጋለጡትም ይገኛሉ።
እነዚህ ድርጊቶች በዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን ባለማግኘቱ እና ከአለም አቀፍ የሰው መብቶች ተሟጋች ተቋማትም ተደብቀው እየተፈፀሙ ሲሆን፤ በስልጣን ላይ ያለው የፋሺስት አብይ ቡድንም በመሳሪያ አፈ-ሙዝ የኦሮሞን ሕዝብ ለማንበርከክ እና ለሕዝቡም ያለውን ንቀት በይፋ በማሳየት ላይ ይገኛል። ይህም ድርጊት ቤት ንብረታቸውንም ከማቃጠል አልፈው በገዛ ቁዬአቸው ላይ ምን ያደርጉኛል በማለት በቤተሰብ ፊት ጥይት በማርከፍከፍ ልጆችንም ሆነ ወላጆችን በመረሸን ላይ ይገኛል።
በዚህም መሰረት መጋቢት 27/2024 በደቡብ ምዕራብ ሸገር፣ በቶሌ ወረዳ ሶምቦ እና ጫንጮ ቀበሌ ውስጥ ኦቦ ሙለታ ደበላ የሚባሉትን ጥይት አዝንበውባቸው ከገደሉዋቸው በሗላም ቤታቸዉን ከእነ ንብረቱ አቃጥለው አውድመውታል። በዚህም ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ሃዘናቸዉን ያለ መጠለያ እንዲወጡት ተገድደዋል።
ከዚህም ሌላ የኦቦ አሹ Dhuጉማ አራት ቤቶችን እና የኦቦ ሻምቡ ቲቶን ደግሞ ሁለት ቤቶቻቸዉን ከሙሉ የቤት እቃቸው ጋር አቃጥለው ማውደማቸውን ነዋሪዎች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
የአካባቢው ነዋሪዎችም አክለው የፋሺስቱ ብልፅግና ታጣቂ ቡድን አላማ የኦሮሞ ህዝብ ምጣኔ ሀብትን ማዉደም እና ለሕዝባችን የዓይን ብሌን የሆኑትን እንቁ ልጆች ላይ በማነጣጠር ግድያ መፈጸምም መሆኑን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግረዋል።
ምንም እንኳን ንብረት መዝረፉን፣ ቤት ንብረት ማቃጠሉንም ሆነ ግድያውን የሚፈፀመዉ የፋሺስት አብይ የብልፅግና ታጣቂዎች ቡድንም ቢሆን የዚህ ድርጊት ወጣኞችና ዉሳኔ ሰጪዎች ከወረዳው አስተዳደር ክፍል እንደሆነና አላማቸውም በወረዳዉ የሚኖሩትን ኦሮሞዎች ስነልቦና ለመስበር እና አንበርከኮ ለመግዛት እንደሆነም ነዋሪዎቹ ገልፀዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት፣ እና ንጹሃን ኦሮሞን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ለማዘዝ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
