ሚያዚያ 20/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በኦሮሚያ ተሰማርተው ያሉት የፋሺስት አብይ ብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የሚፈፅሙት ኢሰብአዊ ድርጊቶች የኦሮሞን ህዝብ ለድህነት የሚዳርግ እና የወደፊት ህልዉናዉን አስጊ ደረጃ ላይ የሚያደርስ መሆኑ ተደርሶበታል።
የፋሺስቱ ቡድን ጦሩን በማሰማራት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዉስጥ ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአርሶ አደር መኖሪያ ቤቶችን በማቃጠል ቤት አልባ በማድረጉ ሕዝቡ በአካባቢው በሚገኙ ሜዳዎች እና ጫካ ዉስጥ ለመኖር ተገድደዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን ሞልቶ ተርፎዋቸው ይኖሩ የነብሩ ዛሬ ለዕለት ጉርሳቸው የሰውን እጅ እያዩም ይገኛሉ።
በተለይም ካለፈው አመት ጀምሮ በምዕራብ አርሲ ዞን በገደብ ሀሳሳ ወረዳ የንፁሀን ዜጎች ቤት በመቃጠሉ ብዙ ቤተሰቦች ለከባድ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ።
መጋቢት 24/2024 በዚሁ ወረዳ የብዙ አርሶ አደር መኖርያ ቤቶች ከነንብረታቸው በኢምፓየሪትዋ ታጣቂዎች ተቃጥሎዋል። ቤታቸው ከተቃጠለባቸው ሰዎችም መካከል ስማቸውን ያግኘነው፦
- አማን በdhaሶ፣
- አቡነ በdhaሶ፣
- ፋይዩ በdhaሶ፣
- በdhaሶ ሃጂ ፋኖ፣
- በdhaቱ ጋለቶ፣
- አብደኔ በdhaሶ፣
- አብዶ ሀጂ ፋኖ፣
- አማዶ ሎሎ፣
- ገለቶ ሎሎ፣
- ሙዲ ቡርቃ፣
- አሺም ሙዲ፣
- ቶላ ሙዲ፣
- ባከሮ ሌንጂሶ፣
- አብዱራህማን ጋሪዮ፣
- ሄዶ ሾላ፣
- ሀጂ ቱፋ፣
- ሀጂ ጊሼ፣
- ሀጆ ጊሼ፣
- ሀሰን ጂሎ፣
- ጂሎ ኮርሬ፣
- ሀጂያ ገነሞ እና
- በሺሮ ኩሪ ይባላሉ።
እነዚህም ቤታቸው በእሳት የወደመባቸው ሰዎች ከእርሻ ስራ በሚያገኙት ገቢ ቤታሰቦቻቸውን የሚያስተዳድሩ የፖለቲካ ተሳትፎ የሌላቸው አርሶ አደሮች ሲሆኑ፣ በወረዳው የተሰማሩት የፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች ግን ለማዉደማቸው የሰጡት ሰበብ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትደግፋላችሁ የሚል ተአማኒነት የሌለው ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎቹ ለአራት ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ገልጸዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
