ሚያዚያ 29/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ደቡብ ምሥራቅ ዞን ጪብራ ጃል ነdhi ገመዳ እና ጪብራ ማዳ-ወላቡ በጥምር ሆነው፣ ኦነሰን ለማሰስ ዘመቻ በሚል በተሰማራው የማፍያው ብልጽግና ጦር ቡድን ላይ በወሰዱት የደፈጣ ወታደራዊ እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው ታውቋል።
ይህንኑም የማጥቃት እርምጃ ያካሄዱት ሚያዚያ 7፣ 2024 ከቀኑ 11:00 ሰዓት እስከ 12:30 በምስራቅ አርሲ፣ ሲርካ ወረዳ፣ገለቤ አማጃ ቀበሌ ቡርኩቱ በሚባል ስፍራ ሲሆን፣ በተወሰደው እርምጃም ከአብይ አህመድ ጦር 5ቱን በሞት 7ቱን ደግሞ ማቁስሉ ታዉቋል። እንደ መብረቅ የወረደባቸው የደፈጣ ጥቃት የማፍያው ብልፅግና ጦር ሙትና ቁስለኞቻቸውን ሳያነሱ ፈርጥጠዉ ሄደዋል።
በጽኑ አላማ እንቁ ህይወቱን ለሕዝቡ እና ለሐገሩ ነፃነት መስዋዕት ለመሆን የሚታገልን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ማሸነፍ እንደማትችል ገብቶህ ተገድደህም ሆነ በውዴታው ፋሺስት አብይን ለማንገስ የምትታታረው የብልፅግና ጦር ቡድን 11ኛው ሰዓት ላይ ደርሰሃልና የያዝከዉን መሳሪያ አስቀምጠህ ህይወትህን አትርፍ እንላለን።
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ!
