• Wed. Oct 7th, 2026

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን፣ ሚኤሶ ወረዳ ሁለት ወጣቶችን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊ ናቸው በሚል ሰበብ ታስረው እየተሰቃዩ ይገኛል 

May 5, 2024

ግንቦት 3/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

በአከባቢው የሚንቀሳቀሰዉ የብልፅግና ጦር ቡድን እና የወረዳው ካቢኔዎች ለኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድጋፍ እየሰጣችሁ ነው በማለት ኦሮሞን በጅምላ እያሰቃዩና እየገደሉም መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል::

የኢትዮጵያ ኢምፓየር ጦር እና ካቢኔው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ይደግፋሉ በሚል ሰበብ በመላው ኦሮሚያ ሰላማዊ ዜጎችን ሲያሰቃዩና ግድያን ሲፈፅሙባቸው ይስተዋላል::

በሚኤሶ ወረዳ፣ ሚኤሶ ከተማ ውስጥ ሚያዚያ 14፣ 2024 ኢድሪስ ዩሱፍ እና አሂመድ የተባሉ ሁለት ወጣቶች የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊ ናቸው በሚል በብልፅግና ጦር ቡድን ተይዘው ወደ ጪሮ ከተማ ተወስደው መታሰራቸውንና እያሰቃዩዋቸውም እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች አሳውቀውናል።

እነዚህም ወጣቶች በፖለቲካ ውስጥ ምንም ሚና እንዳልነበራቸው እና በጥርጣሬ ብቻ ያለምንም የህግ ከለላ  መታሰራቸውን ነዋሪዎቹ አክለውም ገልጸውልናል ።

የወረዳው ካቢኔ በከተማዋ የምትኖር ቀሬ ሀምዲያን እና ሌሎችንም በገንዘብ በመግዛት እነሱንም ህብረተሰቡ ውስጥ በማሰማራት ለመሰለልና የፋሺስቱን ብልፅግና ቡድን ባለመደገፋቸው ብቻ በጥርጣሬ ጠቁማ ብዙ ሰላማዊ ኦሮሞዎችን በቁጥጥር ስር እንዳስዋለች ታውቆዋል። ስለዚህም ከዚህች ቃሬ እና ከመሰሎቿ ራሳቸሁን እንድትጠብቁ አናሳስባለን::

ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading