ግንቦት 4/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነሰ) ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ሰበብ በኦሮሚያ የጅምላ ግድያ፣ ዘረፋና እስራት እየፈጸሙ የሚገኙት የብልፅግናው ታጣቂዎች የኦሮሞን ሕዝብ ንብረት በመዝረፍ እና ከቤቱን ከነንብረቱ በእሳት በማጋየት ለድህነት ከመዳረጋቸውም በላይ ማቆሚያ የሌለው የጅምላ እስራት እየፈጸሙበትም ይገኛሉ።
ሚያዚያ 2፣ 2024 በቄሌም ወለጋ ዞን፣ አንፊሎ ወረዳ፣ ጎቢ ጃሪ ቀበሌ የገበሬዎችን ንብረት በመዝረፍ፣ እስራትና ከባድ ድብደባ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተፈጽሟል።
ይህ ድርጊት ከተፈጸመባቸው ውስጥ፦
- ኦቦ መንግሥቱ ቶላ አምስት ኬሻ ቡና ሲዘርፉ
ክፉኛ ድብደባ እና የአካል ጉዳት እስከ እስር የደረሰባቸው፦
- ኦቦ መልካሙ ኢታና እና
- ኦቦ ሚቲኩ ጢኒቲ ታስረዋል።
- አዴ ሹኬ ካባዳ እና
- አዴ ፋጂሪ ታስፋ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተሰምቷል።
የብልፅግናው ታጣቂዎች ያለምንም ተጨባጭ መረጃ እነዚህ ሰዎች ላይ ከፈጸሙት ግፍ በተጨማሪም ሕዝቡ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን እንዳይቀርቡ እና በጥርጣሬም ለመፈረጅ ስልት በመንደፍ ሰላማዊ ዜጎችን እያሰቃዩ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልጸዉልናል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በቅርሰ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት እና የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
