ግንቦት 4፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የብልጽግና ካቢኔ እና ጦር ቡድን በኦሮሞ ህዝብ ላይ አረመኔያዊ ድርጊት እየፈፀሙና ንብረት እየዘረፉ እንዲሁም የኦሮሞ አርሶ አደሮችን ቤት እያቃጠሉ የአካባቢው ህዝቦች በሐዘንና በለቅሶ ድባብ እንዲዋጡ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።
በምስራቅ ሸገር ዞን ፈንታሌ ወረዳ፣ በሃሮሬቲ መንደር ውስጥ የአገዛዙ የጦር ቡድን ለኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ድጋፍ እያደረጉ ነው በሚል ስበብ የህዝቡን ንብረት መዝረፋቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል::
በእነዚህ የብልፅግና ጦር ቡድን ንብረታቸው የተዘረፉ ሰዎችም፦
1. ከ ሺቶ አማኖ 4 ፍየሎች፣
2. ከ መሀመድ ቱፋ 8 ፍየሎች፣
3. ከ ጀማል ቱፋ 1 ፍየል፣
4. ከ Dhiታ ዋሪዮ 2 ፍየሎች፣
5. ከ አብዱራህማን ማመድ 2 ፍየሎች፣
6. ከ ኡቱዩ ሲሪ 3 በጎች፣
7. ከ ሱልጣን አማድ 3 በጎች፣
8. ከ ዋቆ ቦሩ 1ፍየል፣
9. ከ አሻ ጂማ 3 ፍየሎች፣
10. ከ ሱልጣን ጂማ 2 ፍየሎች፣
11. ከ ሁሴን ጂማ 3 ኩንታል ጤፍ፣
12. ከ ሁሴን ገለቶ 3 ኩንታል ጤፍ እና
13. ከ ፊራኦል አብዱሰላም 8,000 ብር ጨምሮ ሙሉ ንብረቱን ዘርፈዋል።
እንዲሁም፦
14. የ አምቦ አባቱን ማጓጓዝ የሚችሉትን ንብረታቸውን ዘርፈው ያልችሉትን ደግሞ ከቤታቸው ጋር በእሳት ማጋየታቸዉን ምንጮቻችን ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ዘግበዋል።
ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በማዉደም ለረሃብ፣ ለእርዛት እና ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

