• Sat. Oct 10th, 2026

በምዕራብ ሸገር ጀልዱ ወረዳ የኮሎኔል አብይ አህመድ ጦር ቡድን ሁለት ቄሮዎችን በጥይት ደብድበው ገድለዋል

May 8, 2024

ግንቦት 7/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

“ከቅርብ ግዜ ወዲህ በጀልዱ ወረዳ እየተፈጸመ ያለው ግድያ በዘር ማጥፋት ላይ ያነጣጠረ ነው።” ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎችና የተለያዩ ምንጮች ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ለአቢኦ) ገልጸዋል።

“ሐገር አስተዳድራለሁ” ባዩ ፋሺስቱ አብይ አህመድ፣ ያደራጀው የብልጽግና ፓርቲና የጦር ሃይሉ በሰላማዊ ኦሮሞዎች ላይ ባነጣጠረው ዘመቻው ኦሮሞን በጅምላ መግደል፣ መዝረፍና ቤት ንብረታቸውን ማቃጠል ላይ እተኩሯል። ይህ የሽብር ጦር ዘመቻ በኦሮሞ ሕዝብ ህልውና ላይ ያነጣጠረ በመሆኑ አሳሳቢና ድርጊቱም ወደ ጥፋት ሊያመራ የሚችል መሆኑን ከወዲሁ ይጠቁማል።

መጋቢት 31፣ 2024 በምዕራብ ሸገር ጀልዱ ወረዳ ሳሪቲ ድንቄ ቀበሌ ውስጥ ሁለት ቄሮዎችን፤ ወልተጂ መርጋ ጉታ እና ዲሪባ ጫላ ሰቦቃ ተብለው የሚጠሩ ግለሰቦችን እነዚሁ የገዢው ቡድን ታጣቂዎች ወደ መኖርያ ቤታቸው በመምጣት ይዘዋቸው እንደሄዱና በመንገዳቸውም ጥይት እንደ ዝናብ በላያቸው ላይ በማርከፍከፍ ገድለው መንገድ ላይ ጥለዋቸው እንደሄዱ የአከባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።

ቄሮዎቹ ከአርሶ አደር ቤተሰብ የተወለዱ እና ቤተሰቦቻቸውን በግብርና በመርዳት የሚኖሩ ሰላማዊ ልጆች ነበሩ። የብልፅግና ገዳይ ጦር ቡድን ያለ ምንም ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ቤት አውጥተው መንገድ ላይ ገድለው ጥለዋቸው ሄደዋል።

በዚሁ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች (መንደሮች) ውስጥ በርካታ ንፁሀን ኦሮሞዎች እየተገደሉ፣ ቤታቸው እየተቃጠለ እና የጅምላ እስራትም እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ምንጮቻችን ነግረዉናል።

ከዚህም በላይ መጋቢት 31፣ 2024 ኦቦ ገመቹ ሂርኮ የተባሉትን ሰላማዊ አርሶ አደር ይዘው እስር ቤትም ከትተዋቸዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ማድረግ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading