• Thu. Oct 8th, 2026

በምስራቅ ሸገር በመቂ ከተማ ውስጥ የብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች አንድ ሰላማዊ ሰው ከቤቱ በመያዝ የት እንደደረሰ ደብዛውን አጥፍተውታል

May 6, 2024

ግንቦት 5/2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

በፋሺስቱ አብይ አህመድ የብልፅግና ቡድን አገዛዝ ስር በአስከፊ ስቃይ ውስጥ ያለው የኦሮሞ ህዝብ ለዚህ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሕዝብ የማይገባው ኢ-ፊትሃዊ ድርጊት እየተፈጸመበት ይገኛል። ”ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ” በሚል ሰበብ ብዙዎችን ከገዛ ቀዬቸው ታፍነው እየተውሰዱ ደብዛቸዉን ማጥፋት የተለመደ አሰራር በመሆኑ እነኝህ የዚህ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች በህይወት ይኑሩ አይኑሩ ለማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል።

ሚያዚያ 1፣ 2024 በምስራቅ ሸገር ዞን፣ ዱግዳ ወረዳ፣ በመቂ ከተማ የ03 ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የሆኑት ኦቦ ግርማ ጃራ የሚባሉት ግለሰብን እነዚሁ የፋሺስት አብይ ብልጽግና ጦር ቡድን ቤታቸው ውስጥ በመግባት ፍተሻ ካካሄዱ በኋላ እናገኛለን ብለው ያቀዱትን ስላላገኙ ሌላ ምክንያት በመፍጠር፣ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር የስራ አስፈፃሚ አባል የነበሩት ጃል በቴ ኡርጌሳ የአንተ አማች አይደለም ወይ? ስለሆነም ስብሰባ በሚጠሩህ ጊዜ ትመጣለህ በማለት ከቤታቸው ወስደው የት እንዳደረስዋቸው ማወቅ አለመቻሉን የአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ምንጮች ተናግረዋል።

እንዲሁም እቤታቸው እያሉ ካነሱባቸው የዉንጀላ ንግግሮች አንዱ “አንተ በገንዘብ ድርጅታችንን ወይም ፓርቲያችንን እየደገፍክ አይደለም። ይኸዉም በአጠቃላይ የሚያመላክተው አንተ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ደጋፊ ነህ” እያሉ በተደጋጋሚ የወነጀልዋቸው ሲሆን፣ ይሄ ድርጊት ሆን ተብሎ እሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ችግር ውስጥ ለማስገባት አቅደው የጀመሩት ነው ሲል ምንጫችን በተጨማሪ ዘግቦአል።

እሳቸውም በእድሜ የገፉ፣ በሕዝቡም የተወደዱና የተከበሩም የሐገር ሽማግሌ ሲሆኑ በፖለቲካ ውስጥም ምንም ሚና ያልነበራቸው እንዲሁም መደበኛ የዕለት ዕለት ስራቸውን የሚሰሩ ሰው መሆናቸውን ምንጮቻችን አክለው ነግረውናል። በእኚህ ትልቅ ሰው ላይ የተፈፀሙት ድረጊቶች በከተማው ውስጥ በተደጋጋሚ በሌሎች ኦሮሞዎች ላይም እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ፋሺስት አብይ አህመድ ፋሺስታዊ ስልት በመንደፍ የእድሜ እርከንም ሳይገድበው በሚመራውና በሚያዝዘው የብልጽግና ጦር ቡድን ኦሮሞን ለማጥፋት ተዘጋጅቷል። ኦሮሞ ከእንግዲህ ምንም ግዜ ሳይወስድ በአንድ መንፈስ እና በቆራጥ አቋም ይህን የፋሺስት ቡድን ከጫንቃው ማራገፍ አለበት እንላለን። 

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading