ግንቦት 9፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የደቡብ ምሥራቅ አውራ የሆኑት የጀግኖቹ ጭብራ ሌንጂሶ ዲጋ እና ጭብራ ጃል ነdhi ገመዳ ሚያዚያ 14፣ 2024 ከምሽቱ 5:30 ሰአት ጀምሮ በተለያዩ ቦታዎች በአሰሳ ስም የተሰማራውን እና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሽብርን በሚያካሂደው የፉሺስቱ የብልፅግና ጦር ላይ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ አኩሪ ድልን ተጎናጽፈዋል። ድሉንም እንደሚከተለው እንተነትለዋለን።
ጋሻ እና መከታ የሆነው ጭብራ ጃል ነdhi ገመዳ
በምሥራቅ ሸገር ዞን፣ አዳማ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ፣ አሉቶ ቀበሌ፥ 20 የጠላትን ጦር ሲገድል 8ቱን አቁስሎ የተረፉት ደግሞ በተለያየ አቅጣጫ መፈርጠጣቸው ታውቆአል።
በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ፣ ቦሬ ቀበሌ፥ 35 የጠላትን ወታደር ሲገድል 40 ደግሞ አቁስሏል። ከነዚህም ውስጥ የመቶ አለቃው (ajajaa) ዮሴፍ ቆስሎ በህክምና ላይ እንዳለ ህይወቱ ሲያልፍ፣ አንድ የ 50 አልቃም (ajajaa) መሞቱ ታውቆዋል።
ጋሻ እና መከታ የሆነው ጭብራ ሌንጂሶ ዲጋ
በምሥራቅ አርሲ ዞን፣ ጃጁ ወረዳ፣ ሶቄ ቦቂቻ እና ዉሩታ ዶሪ ቀበሌዎች፣ ኢሼቴ በተባለው የጠላት ጦር ካምፕ ላይ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ አስራ አንዱን ገድሎ 16ቱን ደግሞ አቁስሎ የተረፉትም ካምፑን እንዲለቁ አድርጓል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በዛው ሌሊት በምሥራቅ ሸገር ዞን፣ ፈንታሌ ወረዳ፣ ጋረ ዲማ ቀበሌ ውስጥ ጠላት በሰፈረበት ካምፕ ዉስጥ ወደ ላይና ወደ ታች አሯሩጦ 8ቱን በሞት ሲቀጣ፣ 11ን ክፉኛ አቁስሎ፣ በርካታ የጦር መሳሪያዎችንም በማስፈታት ለኦሮም ነፃነት ትግል ገቢ አድርጓል።
በአጠቃላይ ጀግናው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የጀግኖች ቀን በዓልን ሚያዚያ 15፣ 2024ን ምክንያት በማድረግ “ብድር በምድር” የሚለውንም መርሆ በማንገብ ጠላትን እንቅልፍ በመንሳት እና እርስ በእርሷ እንድትፈራራና በተለያየ አቅጣጫ እንድትሸሽ አድርርት ዉሎአል።
የብልጽግናው ቡድን ፕሮፖጋንዳ በተግባር ይከሽፋል!
ድል ለኦሮሞ ሕዝብ እና ለጭቁን ብሔር ብሔረሰቦች!
