• Sat. Oct 10th, 2026

በሰሜን ኦሮሚያ፣ በወሎ ዞን፣ ዱጉጉሩ ወረዳ የፋሺስቱ አብይ አህመድ ብልፅግና መዋቅሮች ሰላማዊ ኦሮሞዎችን እያሰሩና ህብረተሰቡንም እየሸበሩ መሆናቸው ታውቋል

May 11, 2024

ግንቦት 8፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)

የኦሮሞ ህዝብ ነፃነት ትግልን በማራመድ ላይ የሚገኘውን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ትመግባላችሁ፣ መንገድ ታሳያላችሁ እና መረጃም ታቀብላላችሁ በማለት ሽፍታው የብልጽግና ቡድን የኦሮሞን ሕዝብ ማስፈራራትና ማሰቃየትን መደበኛው የዕለ ዕለት ስራው አድርጎ በማከናወን ላይ ይገኛል።

ሚያዚያ 4፣ 2024 በሰሜን ኦሮሚያ በወሎ ዞን፣ ዱጉጉሩ ወረዳ ጋንጃ ቀበሌ የፋሺስቱ ብልፅግና መዋቅሮች የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ወደዚህ አካባቢ እንዲመጣ እያደረጋችሁ ያላችሁት እና መንገድም እየመራችሁ ያላችሁት እናንተ ናችሁ በማለት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ከባድ ድብደባ ከፈጸሙና ካስፈራሩ በኋላ ሰዉ በማስታረቅ የሚታወቁትን መሀሐመድ አሂመድ ሃጂ (አባ Dhiራ) የተባሉትን አዛዉንት በጋንጃ ቀበሌ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ይዘዉ መሄዳቸውንም የአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል።

የእድሜ ባለጸጋው አባ Dhiራ ምንም የፖለቲካ አስትዋፅኦ እንደሌላቸውና በአከባቢዉም የተከበሩና አስታራቂ ሽማግሌ በመሆናቸው፣ መታሰራቸው በአከባቢዉ ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ  ቅሬታ መፍጠሩንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዉልናል::

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ ያለምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ማሳሰር፣ በእስር ቤት ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ፣ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”

Leave a Reply

Discover more from Qeerroo Bilisummaa Oromoo

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading