• Tue. Nov 24th, 2026

በምስራቅ ጉጂ ዞን፣ በዋደራ ወረዳ አንዲት የኦሮሞ ቃሬ በሰው በላው የብልፅግና ቡድን ጦር ታርዳ፣ ያለፈው ዘግናኝ  የምኒሊክ አረመኔያዊ አገዳደል በ21ኛው ክፍለ ዘመን ተፈጥጽሞባት፣ ማለትም ጡቶችዋም ተቆርጠው ተጥላ ተገኝታለች

May 11, 2024

ግንቦት 11፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)   

አረመኔያዊና እና የተረገመ ዓላማ ተላብሰው የተሰማሩት የብልፅግና ቡድን ታጣቂዎች በተሰማሩበት አካባቢ ሁሉ በሰላማዊዉ የኦሮሞ ማህበረሰብ ላይ በየቀኑ አሰቃቂ ድርጊት እየፈጸሙ ይገኛሉ።

መጋቢት 26፣ 2024 በምስራቅ ጉጂ ዞን፣ ዋደራ ወረዳ፣ መርካቶ ቀበሌ ውሰጥ ትኖር የነበረችውን ቃሬ አሚና አሂመድን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለው፥ በጩቤ እንደ እንሰሳ በማረድ ቀጥሎም የሰውነት ክፍልዋን፣ ጡቶችዋን ቆራርጠው፣ ጥለዋት መሄዳቸውን የአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ምንጮች ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ ኢምፖየር ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ልክ እንደ ሚኒሊክ ዘመን፣ ዛሬም በአረመኔው የብልፅግና አስተዳደር ዘመን በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደለ ይገኛል። ዛሬም የኦሮሞ ሴት ወጣቶች ጡት እየተቆረጡ ይጣላል።

ይህች ቃሬ የተገደለችበት ሁኔታ ፍጹም አረመኔያዊና፣ የኦሮሞን ሕዝብ ባህል እና ስብዕና የሚፃረር ድረጊት ሲሆን፣ በታሪክ የምንሰማዉንና የምናነበዉን ሚኒሊክ ሲፈፅም የነበረውን ድርጊቶች የእርሱ የልጅ ልጆች ደግመው መፈፀማቸውን የሚያሳይ መሆኑንም ምንጮቻችን ገልፀዋል።

ፋሺስት አቢይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦

“የኦሮሞን ሕዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”

Leave a Reply