ግንቦት 12፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኦሮሚያ ሲኖዶስ “መንበረ ጴጥሮስ” በይፋ ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ የኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን መዋቅር በኢትዮጵያ ኢምፓየር ውስጥ እየተናወጠ መሆኑ ይነገራል።
የኦሮሞ ህዝብ የራሱን ሲኖዶስ ማቋቋሙ ህጋዊ መብቱ ቢሆንም የሚኒሊክ ስርዓት ደጋፊዎች በቋንቋችሁ እና በማንነታችሁ መኖር አትችሉም በማለት በኦሮሚኛ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩ አባቶችን ሲከለክሉና በተለያየ ጊዜ ሲያሳስሩ የነበሩ ሲሆን፣ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ይህንን እኩይ ድርጊታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
በቄሌም ወለጋ ዞን፣ ደምቢ ዶሎ ከተማ ሚያዚያ 5፣ 2024 ከፊንፊኔ ከመጡት የኢምፓየሪቱ ሲኖዶስ አባሎች እና በደምቢ ዶሎ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሚያ ሲኖዶስን የሚደግፉ ምዕመናን መካከል በተከሰተው ግጭት የፋሺስቱ ብልፅግና ጦር ቡድን 10 ኦሮሞዎችን በመያዝ ያሰረ መሆኑ ታውቋል።
የኦሮሞ ህዝብ በራሱ ቋንቋ የእግዚአብሔርን ቃል ለመማር እና ለማምለክ የሚገባውን መብቱን ለረጅም ጊዜ ቢጠይቅም ከኢምፓየሪትዋ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትሪያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት መልስ ባለማግኘቱ እስከ ዛሬ ድረስ ጥያቄያቸው እንዳልተፈታ የደምቢ ዶሎ ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
የፋሺስት አብይ አህመድ ኢምፓየር ጦር የኦሮሞን ሕዝብ ህልውና ለማጥፋት የተደራጀ ኃይል እንጂ ስሙ እንደሚያመለክተው የሐገር እና የሕዝብ መከላከያ አይደለም።
