ግንቦት 13፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የኢትዮጵያ ኢምፓየር በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው እንግልትና ግድያ ተባብሶ መቀጠሉን ከተለያዩ ምንጮች መረጃዎች እየደረሱን ነው። የኢምፓየሩ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት “Koree Nageenyaa” ማለትም የሰላም ኮሚቴ በማለት ተሰይሞ የተቋቋመው ኮሚቴ የኦሮሞን ህዝብ በግልጽና በስውር በጭካኔ እየገደለ ይገኛል።
በንጹሃን ላይ የሚፈጽሙትን ግድያ አጠናክረው በመቀጠል ሚያዚያ 3፣ 2024 በደቡብ ምዕራብ ሸገር ዞን፣ ሰበታ ሐዋስ ወረዳ፣ ዮሐንስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ንጋት ላይ 12 ሰዓት አካባቢ የግለሰቦች ቤት ውስጥ በመግባት ሁለት ቄሮዎችን የገደሉ ሲሆን ሶስተኛውን ይዘውት መሄዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ነግረዋል።
በማፍያው ብልጽግና ታጣቂዎች የተገደሉት ቄሮዎች ታዱ ሐምዴና ገመቹ የሚባሉ ሲሆኑ ጅሩ ጫላ የተባለውን ቄሮ ከባድ ድብደባ ካደረሱበት በኋላ ይዘውት ሄደዋል።
በዚሁ ወረዳ፣ በከለቻ ከተማ፣ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አባባቾ አበራ የተባሉ ግለሰብ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አለህ በማለት ከቤቱ አስወጥተው የግለሰቡን ቤት የጦር ካምፕ አድርገው እንደሰፈሩበት የአካባቢው ነዋሪዎች አሳውቀውናል።
በዚህ ምክንያት የአባባቾ ቤተሰብ በየቦታው ተበታትነው በችግርና በስጋት ላይ እንደሚገኙ የአቢኦ ምንጮች ተናግረዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ ንብረትና ቤት በመውረስ ከዚያም አልፎ ቤታቸውን ለጦሩ ካምፕ በማድረግ ለረሃብ፣ ለእርዛት፣ ለመጠለያ አጥነት አጋልጦ ለመግዛት፣ እና ንጹሃን ኦሮሞን በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ ለማዘዝ መንበር የተሰጠው የፋሺስታዊ መንግስት መሪ።”
