ግንቦት 21፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
የፋሺስቱ ብልፅግና ቡድን በሰላማዊ ኦሮሞዎች ላይ የሚፈጽመው አሰቃቂ ድርጊቶች፣ የጅምላ ግድያንም አክሎ “አጥፍቶ መጥፋት” የሚለውን መርሆ የተከተለ ይመስላል። “ኦሮሞ መሆን ወንጀል” እየሆነ በሄደበት የብልፅግና አገዛዝ ዘመን በምሥራቅ እና በምዕራብ ጉጂ ዞኖች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች ከቤታቸው ወጥተው ለመመለስ ምንም ዋስትና እንደሌላቸው በመገንዝብ ይህም እጅጉን እንደሚያሳስባቸው ለአቢኦ ገልፀዋል።
እስራትና ስቃይ
ሚያዚያ 22፣ 2024 በምሥራቅ ጉጂ ዞን፣ ሶራ ወረዳ፣ ከበርሲሳ ገሎ ቀበሌ ሶስት ቄሮዎችን፦
- ደሱ ግዛቸው፣
- አለሙ ባነታ እና
- ጉዲና ገመዳ በሃሰት በመወንጀል አስረው እያሰቃዩዋቸው እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
አሰቃቂ የጅምላ ርሸና
- በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲን የጦር ካምፓቸው አድርገው የተቀመጡት የፋሺስት አቢይ ብልፅግና ጦር ቡድን በጅምላ ካምፓቸው ውስጥ አስረው ከሚያሰቃዩዋቸው ንፁሃን ኦሮሞዎች መሃከል 25ቱን ሚያዚያ 12፣ 2024 ከዩኒቨርሲቲው የጦር ካምፕ በሌሊት አውጥተው ወደ ቡሌ ሆራ ወረዳ፣ መዶ በተባለ ቦታ ሁሉንም አንድ ላይ ተረሽነው እንዳገኙዋቸው ቤተሰቦቻቸው ለአቢኦ ተናግረዋል።
- ሚያዚያ 16፣ 2024 በምዕራብ ጉጂ ዞን፣ ቡሌ ሆራ ወረዳ፣ ቡዳ መጋዳ ቀበሌ፣ ሄሬዲ ደራሮ በተባለው መንደር ውስጥ ይኖሩ የነበሩትን ኦቦ ቴሲሳ አርቦ መጋዶን በባለቤታቸዉ ፊት ካስፈራሩዋቸው በኋላ በባለቤታቸ እና በቤተሰቦቻቸው ፊት በጥይት ደብድበው የገደልዋቸው ሲሆን፣
- ሚያዚያ 17፣ 2024 በዚሁ በቡዳ መጋዳ ቀበሌ፣ ሁለት ቄሮዎች፦ ደምበላ ሰፋዪ እና ተስፋዬ ኮሞዶ የሚባሉ ያለምንም ጥፋት ጥይት አዝንበውባቸው እንደገደሏቸው ምንጮቻችን ዘግበውልናል።
የቤትና ንብረት ውድመት
የሰው በላው የብልፅግና ስረዓት ሰራዊት ሚያዚያ 16፣ 2024 በምዕራብ ጉጂ፣ ዱግዳ ዳዋ ወረዳ፣ ገለዴ ቀበሌ ውስጥ የአራት ንፁሃን ኦሮሞዎችን ንብረት ጭነው ለመውሰድ የሚችሉትን ዘርፈው የቀረውን ደግሞ ከቤታቸው ጋር በእሳት አጋይተው አውድመውባቸዋል።
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ አመራር፣ ፕሬዜዳንቱን እና የቦርድ አባሎቹን ጨምሮ ዩኒቨርሲቲውን ለፋሺስት አብይ አህመድ ብልፅግና የጦር ቡድን ካምፕ እንዲሆን መፍቀዳቸው እና ለዚህ አሰቃቂ የዘር ማጥፋት ድርጊት ተባባሪ መሆናቸው ተጠያቂም እንደሚሆኑ ያውቁ ይሆን?
