ግንቦት 22፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ሳዮ ኖሌ ወረዳ፣ፊልፊል ገላን ቀበሌ
የብልጽግና ስርዓት ኦሮሞዎችን አፍኖ አድራሻቸውን የማጥፋት ድርጊቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ምንጮቻችን ከሳዮ ኖሌ ወረዳ ግንቦት 20፣ 2024 ገልፀውልናል። በዚሁ መሰረት ከፊልፊሊ ገላን ቀበሌ ኦቦ ተስፋዬ ታፈራ የተባሉት የልማት ሰራተኛን መጋቢት 25፣ 2024 ከባድ ድብደባ ከፈፀሙባቸው በኃላ በወረዳው እስር ቤት ሲያሰቃዩዋቸው ከቆዩ በኋላ በቅርቡ ከእስር ቤት አውጥተው እንደሰወሩዋቸው ምንጮቻችን ከላይ በተገለፀው ቀን አሳውቀውናል።
ቆንዳላ ወረዳ፣ ገሚ ጋባ ቀበሌ
ሚያዝያ 25፣ 2024 አቦ መሀመድ አቶሞ፣ ባጃጅ ለመግዛት የሚያስፈልጋቸውን ገንዘብ ይዘው ከገጠር ቤታቸው ወደ ከተማ እየሄዱ ሳለ በፋሺስቱ ብልጽግና ቡድን ወታደሮች ከመንገድ ላይ ተይዘው ወደ መኖሪያ ቤታቸውም መልሰው በመዉሰድ “ይህን ሁሉ ገንዘብ ከየት አመጣህ?” ብለው ከጠየቁዋቸው በኋላ በጥይት በመደብደብ ገድለዋቸዋል።
አቦ መሀመድ አቶሞን ከገደሉዋቸው በኋላ በእጃቸው የነበረውን ገንዘብ ወስደው ሴት ልጃቸው በላያቸው ተደፍታ እያለቀሰች እያለ በምን ምክንያት ታለቅሺያለሽ ብለው ሰይፋቸውን ወርውረው ደረትዋን መትተዋት አእምሮዋንም እንደሳተች የአካባቢው ነዋሪዎች አክለው ለአቢኦ ገልፀዋል።
ፋሺስት አብይ አህመድ አሊ በታሪክ ማህደር የሚታወሰው፦
“የኦሮሞን ሕዝብ መዝረፍ፣ ከዚህም እልፎ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲገደሉ እና ለዱር አራዊትም እንዲጣሉ ትዕዛዝ የሚሰጥ የ አውሬነት ባህርይ የተላበሰ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኤምፓየሪትዋ ያስተናገደች፣ ሰብዓዊነት የጎደለው የለየለት ጨካኝ አምባገነ መሪ ነው።”
