ግንቦት 25፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ፋስሽቱ የብልጽግና ቡድን በመላው ሐገሪቷ ባቀጣጠለው ጦርነት አብዛኛው የጦር ሃይሉ እንደወደመበት ይታወቃል። ይህንን ጉደለቱን ለመተካት በመላው ኦሮሚያ ዞኖች እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ታዳጊ ህጻናትን ጨምሮ ለብሔራዊ ውትድርና በግዳጅ በገፍ አፍኖ ወደ ማሰልጠኛ በመውሰድ ላይ ሲሆን፣ አረጋውያን አባቶችን ደግሞ በግዳጅ በሚልሻነት ለማሰማራት ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ምንጮቻችን ነግረውናል።
በዚሁ መሰረት ሚያዚያ 5፣ 2024 በቦረና ዞን፣ ዱቡልቅ ወረዳ፣ በቀርሳ ዳምቢ፣ ጎሮ ዳዳ እና ቀርሳ ዳንቢ ከሚባሉት ቀበሌዎች ከእያንዳንዱ ቀበሌ 21 እድሜያቸው የገፉ ወንዶችን ለሚሊሻነት እና 21 ወጣቶችን ለ ፋሺስት አብይ ብልፅግና የፈራረሰን ሰራዊት ለመጠገን በግዳጅ እየያዙ እንደሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአቢኦ ገልፀዋል።
የግዳጅ ወታደራዊ ምልምላውን እና ከእያንዳንዱ ቀበሌ በግዳጅ መታፈስ ያለባቸውን የቄሮዎች ቁጥር ወሳኝ እና የቀብሌዎቹን ሊቀመንበሮች ትዕዛዝ ሰጪ ገልማ ዲዳ የተባለው የድቡልቅ ወረዳ አስተዳዳሪ መሆኑም ታውቋል።
ከዚህም በላይ የፋሺስት ብልፅግና ቡድን በወረዳው ውስጥ ከኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ጋር ግንኙነት አላችሁ በማለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኦሮሞዎችን አስረው እያሰቃዩ መሆኑን የእከባቢው ነዋሪዎች አክለው ግልፀውልናል።
ኦሮሞ ሆይ ጨቅላ፣ ብሩህ እና የወደፊት ተስፋህና መከታህ ሊሆኑ የሚችሉትን ልጆችህን ከተኩላው የፋሺስት አብይ አገዛዝ ለማዳን በአንድነት ቁም። ጠላቶችህ ስርዓቱን ሙጥኝ ብሎ የሚመራው አብይ አህመድ እና የሰላም ኮሚቴ ተብዬው መሪ ሽመልስ አብዲሳ መሆናቸውንም አትዘንጋ።
