ግንቦት 27፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
ለሆዳቸው የተገዙት በአባ ገዳ ስም እና በሐገር ሽማግሌ ስም የሚነግዱትን ከጎኑ በማድረግ የፋሺስት አቢይ ብልፅግና ቡድን ሚያዚያ 24፣ 2024 በኦሮሞ ሕዝብ ላይ እስከዚህ ዕለት ተደርጎ የማይታወቅ፣ አረመኔያዊ ድርጊቶችን ያዋቀረ እና የረቀቀ ህጋቸውን በጉደር ከተማ ታወጀ።
የፋሺስቱ የብልፅግና ስርዓት የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም የኦሮሞን ሕዝብ የበለጠ ለስቃይ የሚዳርግው እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ቤተሰቦች ላይ የታወጀው አዋጅ ከዚህ በታች ያሉትን ውሳኔዎች በጉደር ከተማ እና በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ማሳለፋቸውንም ተናገሩ።
ድንጋጌዎቹም፦
- የታጋዮችን ቤተሰብ የጎበኘ ሰው፤
- እሳት ማያያዣ (ረመጥ) የሰጠ ው፤
- ምግብ እና ውሃ ያካፈለ፤
- ከእነሱ ጋር ያወራ እና
- ማንኛውም አይነት የማህበራዊ ግንኙነት ከእነሱ ጋር ያካሄደ
10,000 ብር እንዲቀጣ ውሳኔ መተላለፉን ነዋሪዎች ለአቢኦ ተናግረዋል።
በተጨማሪም በጉደር ከተማ እስር ተጠናክሮ በመቀጠሉ ሚያዛ 27 ቀን, 2024 ስማቸው በቀላ ዳንዴሳ፤ መርጋ አንጋሱ እና ሚልኮ የሚባሉ ሰዎች በብልፅግና ጦር ከከተማው ውስጥ በመያዝ በከተማው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እየተሰቃዩ እንዳሉ ታውቋል።
ኦሮሞ ሆይ ይህንን አርመኔ ስርዓት በጊዜ መቅጨት እንዳለብህ አትዘንጋ።
