ግንቦት 27፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO)
በምዕራብ ሸገር ዞን በሚዳ-ቃኚ ወረዳ ውስጥ ፋሺስት እና አረመኔው የብልፅግና ሰራዊት የተመረዘ ምግብ በማስቀመጥ በህብረተሰቡ እና በከብቶች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰማ።
ሚያዚያ 25፣ 2024 የፋሽስት ብልፅግና ሰራዊት በምዕራብ ሸገር ዞን በሚዳ-ቃኚ ወረዳ፣ በካፋ አቤቶ ቀበሌ፣ በበካፋ መንድር ውስጥ ለረጅም ጊዜ ከነበረበት ለቅቆ መውጣቱ አንድ የቀበሌው ነዋሪ ለአቢኦ ተናግረዋል።
በፋሺስት አብይ ትእዛዝ በመርዝ አቅራቢነት፣ እና በራሱ የብልፅግናው ጦር ቡድን መርዝ በሰው ምግብና በመኖ ውስጥ በመጨመር ሞት እና የጤና ጉድለት የደረሰባቸው፦
- የኦቦ ተስፋዬ ቡሹ አምስት ልጆቹ የተመረዘውን ምግብ ከበሉ በኋላ አንዷ ልጃቸው ወዲያው ህይወትዋ ሲያልፍ፣ አራቱ ደግሞ ለከባድ የጤና ጉዳት መጋለጣቸው ታውቆዋል። ሟችዋ ማሬ ተስፋዬ ትባላለች። ኩሜ ተስፋዬ እና ሶስቱ ልጆቻቸው ደግሞ ከባድ የአካል ጉድለትም ደርሶባቸዋል።
- ሰባት የቀንድ ከብቶችም የተመረዘ መኖ ተመግበው ህይዎታቸው እንዳለፈም ታውቆዋል።
የፋሺስት ብልፅግና ሰራዊት ከካምፑ ለቅቀው መውጣት እና ወዲያው ደግሞ ቤት ፍተሻ በማለት በሕዝብ ምግብ ውስጥ መርዝ መጨመር በደምብ በፕሮግራም የተደገፈ ለመሆኑ የኦሮሞ ሕዝብ ሊጠራጠር አይገባውም። ይህም የሚያመላክተው፣ ከብልፅግናው ከፍተኛ አመራር “አሳውን ለማጥፋት ባህሩን ማድረቅ” ማለትም “የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊትን ለማጥፋት የኦሮሞን ሕዝብ ገድሎ መጨረስ” የተባለውን አጣድፈው እውን ለማድረግ አረመኔያዊ ተግባሩን ቀጥሎዋል።
