• Tue. Nov 24th, 2026

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሽኒጋ ቃል-ኪዳን ስምሪት በማወጅ ጠንካራ ውጊያዎችን በኦሮሚያ ውስጥ ሲያካሄድ በዋለው መሰረት፣ በደቡብ ቦረና ዞንም ጠላትን በሙት እና በቁስል ቀጥቷል

Jun 3, 2024

ግንቦት 30፣ 2024 አራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ (ONM-ABO) 

ግንቦት 28፣ 2024 የሽኒጋ ቃለ-መሃላ ዘመቻን ለማሳካት ጀግኖቹ የነፃነት ጮራ አብሳሪዎች የኦነሰ ባወጣው አዋጅ መሰረት በደቡብ ኦሮሚያ ዕዝ በቦረና ዞን፣ በሚዮ ወረዳ ውስጥ ባደረጉት የማጥቃት እርምጃ በጠላት ኃይል ላይ አኩሪ ድልን አስመዝግበዋል።

ይህ በደቡብ ዞን የሚገኘው የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት በሚዮ ወረዳ በተለያዩ ቦታዎች ከባባድ ጦርነት ያካሄደ ሲሆን፣ ዱከሌ፤ ሜጢ፤ እና ጎምቢሳ በሚባሉ ቦታዎች ድል ማስመዝገቡን የዞኑ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አዛዥ ለአራታ ቢዮሌሳ ኦሮሚያ ተናግሯል።

በዚህ ጦርነትም 12 የጠላት ወታደሮችን ሲገድል በርካታ ቁጥር ያላቸውን ደግሞ በማያገግም ቁስለ ቀጥተዋል። ቁስለኞቻቸውንም በሶስት መኪናዎች ሞልተው ለህክምና ወደ ሆስፒታል መውሰዳቸውን አቢኦ ከምንጮቹ ተነግሮታል።

ድል ለኦሮሞ ህዝብ!

Leave a Reply